በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአውሮፓ ሕብረትና የኢትዮጵያ ምርጫ


በአውሮፓ ሕብረት የምርጫ ሪፖርት ላይ ንግግሩ ቀጥሏል፡፡

የአውሮፓ ሕብረት ስለ ኢትዮጵያው የግንቦት 2002 ምርጫ በቅርቡ የሰጠውን ሪፖርት፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አቶ መለስ ዜናዊ የማይረባ በማለት አጣጣሉ። ከአዲስ አበባ የቪኦኤው ፒተር ሃይንላይን እንደዘገበው የአውሮፓ ሕብረት የታዛቢዎች ቡድኑ ኃላፊ በሪፖርቱ ትክክለኛነት በመፅናት፣ "ምርጫው ስልታዊ በሆነ ሁኔታ ተጭበርብሯል" ስለመባሉ ምርምራ እንዲደረግም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለሃገር ውስጥ ጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ የሕብረቱ ታዛቢዎች ቡድን ያወጣው ሪፖርት "የማይጠቅምና እርባና ቢስ በመሆኑ ወደ ቆሻሻ መጣል አለበት" ብለዋል፡፡

አቶ መለስ ሪፖርቱ ስለኢትዮጵያ ሳይሆን "የገዥውን ፓርቲ መጠናከር የማይፈልጉ ኒኦ ሊበራል የሆኑ የምዕራባዊያን አስተያየት ነው" ማለታቸውም ተጠቅሷል፡፡

ባለፈው ሣምንት ብራስልስ ውስጥ ይፋ የሆነው የአውሮፓ ሕብረት የመጨረሻ ሪፖርት የግንቦቱን 2002 የኢትዮጵያ ምርጫ ከተለያዩ አቅጣጫዎች ነው የተቸው፡፡ ከሁሉም በላይ የመንግሥት የኃይል ምንጮች ለገዥው ፓርቲ በሚጠቅሙ መንገዶች በመዋላቸው በብዙ ጣቢያዎች የተመዘገቡት የድምፅ ውጤቶች በታዛቢዎች ከተመዘገቡት የተለዩ መሆናቸውን አመልክቷል፡፡

በስልክ የተጠየቁት የቡድኑ ኃላፊ ታይስ በርማን የሪፖርታቸውን ትክክለኛነት በድጋሚ ያረጋግጡና የጠቅላይ ሚኒስትር መለስን አስተያየት ውድቅ ያደርጋሉ፡፡

ለዝርዝሩ ዘገባውን ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG