በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአውሮፓ ሃገሮች የእየሩሳሌምን መዲናነት ዕውቅና እንደሚሰጡ የእስራኤል ጠ/ሚ ተናገሩ


የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ
የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ

የአውሮፓ ሃገሮች ኢምባሲዎቻቸውን ወደእየሩሳሌም እንደሚያዛውሩ እና ለእየሩሳሌም መዲናነቱዋ ዕውቅና እንደሚሰጡ እምነቴ ነው ሲሉ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ተናገሩ።

የአውሮፓ ሃገሮች ኢምባሲዎቻቸውን ወደእየሩሳሌም እንደሚያዛውሩ እና ለእየሩሳሌም መዲናነቱዋ ዕውቅና እንደሚሰጡ እምነቴ ነው ሲሉ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ተናገሩ።

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ የወሰዱትን ርምጃ ተከትሎ አብዛኞቹ ወይንም ሁሉም የአውሮፓ ሃገሮች ኢምባሲዎቻቸውን ወደእየሩሳሌም እንደሚያዛውሩ እና ለእየሩሳሌም መዲናነቱዋ ዕውቅና እንደሚሰጡ እምነቴ ነው ሲሉ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ተናገሩ።

ኔታንያሁ ብረሰልስ ውስጥ ከአውሮፓ ህብረት የውጭ ፖሊሲ ሃላፊ ፌዴሬካ ሞጌሬኒ ጋር ሆነው በሰጡት መግለጫ ትረምፕ የወሰዱት ርምጃ “ሃቁን ቁልጭ አድርጎ ጠረጴዛው ላይ አስቀምጦታል፣ የሰላም መሰረቱ ሐቅ ነው” ብለዋል።

ሞጌሬኒ በበኩላቸው እየሩስሌምን የሚመለከተው ጉዳይ በእሥራኤልና ፍልስጥኤማዊያን የሰላም ድርድር ውስጥ መፍትሄ እስከሚያገኝ ድረስ የአውሮፓ ህብረት ያለውን ዓለም አቀፍ መከተሉን ይቀጥላል ብለዋል። ያም የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ትረምፕ ባሳለፍነው ሳምንት ያደረጉትን ውሳኔ አለመከተል ነው።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG