በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአውሮፓ ኅብረት የዩክሬን የዓባልነት ጥያቄ ለውይይት ይቀርብ እንደሁ ውሳኔ ይሰጣል


የአውሮፓ ኅብረት ብራሰልስ፣ ቤልጂየም
የአውሮፓ ኅብረት ብራሰልስ፣ ቤልጂየም

የአውሮፓ ኅብረት፤ ነገ ሐሙስ በሚያደርገው ጉባኤ፣ በዩክሬን የዓባልነት ጥያቄ ላይ ይነጋገር እንደሁ ውሳኔ እንደሚሰጥ ይጠበቃል።

ሩሲያ ዩክሬንን መውረሯን ተከትሎ፣ ዩክሬን የአውሮፓ ኅብረት ዓባል ለመሆን ጥያቄ ያቀረበች ሲሆን፣ ምኞቷ ይሳካ እንደሁ የኅብረቱ የዚህ ሳምንት ውሳኔ ፍንጭ ይሰጣል ተብሏል።

ኅብረቱ የዩክሬንን እጩ ዓባልነት ያጸደቀው ባልፈው ዓመት ነበር።

በኅብረቱ የተጠየቁ አብዛኛዎቹን ማሻሻያዎች ዩክሬን መፈጸሟን የአገሪቱ ባለሥልጣናት በመናገር ላይ ናቸው። ዩክሬን ያደረገችውን ጥረት በመመልከት፣ ኅብረቱ አዎንታዊ ውሳኔ ይሰጣል ብለው እንደሚጠብቁ ባለሥልታናቱ ጨምረው ተናገረዋል።

የዩክሬን ኅብረቱን መቀላቀል የምትቃወመው ሃንጋሪ፣ አገሪቱ በጦርነት ላይ በመሆኗ፣ በምትቀላቀልበት ሁኔታ ላይ ንግግር መጀመር የለበትም የሚል አቋም ይዛለች፡፡

የዩክሬን ኅብረቱን መቀላቀልም ሆነ የታሰበውን 54 ቢሊዮን ዶላር ርዳታ በተመለከተ ድምጽን በድምጽ የመሻር መብቷን እናድምትጠቀም ሃንጋሪ አስታውቃለች፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG