የአውሮፓ ኅብረት እና ዩናይትድ ስቴትስ፣ በኢትዮጵያ የተደረሰውን የሰላም ሥምምነት የሚመለከቱት በጥንቃቄ እንደኾነና ከኢትዮጵያ ጋራ ያላቸውን ግንኙነት ወደነበረበት የሚመልሱት በቀስታ እንደሚኾን፣ የአውሮፓ ኅብረት የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ሓላፊ ጆሴፕ ቦረል ዛሬ ተናግረዋል።
ከአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን ጋራ ተገናኝተን ከተወያዩ በኋላ ቦሬል እንደተናገሩት፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ከህወሓት ጋራ የደረሰበት ስምምነት፣ “በዓለም ካሉ ጥቂት መልካም ዜናዎች አንዱ ነው፤” ብለዋል።
ለኢትዮጵያ መንግሥትም ኾነ ለትግራዩ ወገን ያለን መልዕክት፥ ግጭቱ መፍትሔ እያገኘ ያለበትን ሒደት እየተከታተልን መኾኑን እንዲረዱና ግንኙነታችንን ወደነበረበት የምንመልሰው፣ ቀስ በቀስ እና ደረጃ በደረጃ ነው፤”
የአውሮፓ ኅብረት እና አሜሪካ፣ “እጅ ለእጅ ተያይዘው ሥራቸውን በመቀጠል” የሥምምነቱን ተፈጻሚነት መርዳት እንዳለባቸውና፤ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋራ ያላቸውን ግንኙነት ወደነበረበት ስለ መመለስ በተመለከተ ግን፣ በዝግታ የሚደረግ እንደኾነ ቦረል ተናግረዋል፤ ሲል ኤኤፍፒ ዘግቧል።
“ለኢትዮጵያ መንግሥትም ኾነ ለትግራዩ ወገን ያለን መልዕክት፥ ግጭቱ መፍትሔ እያገኘ ያለበትን ሒደት እየተከታተልን መኾኑን እንዲረዱና ግንኙነታችንን ወደነበረበት የምንመልሰው፣ ቀስ በቀስ እና ደረጃ በደረጃ ነው፤” ብለዋል፣ የአውሮፓ ኅብረት የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ሓላፊው ጆሴፕ ቦረል።