በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአውሮፓ ኅብረት የፍልሰት መንስኤዎችን ለመቅረፍ እና የሴኔጋል ልማት ጥረት ለመደገፍ ቃል ገባ


የአውሮፓ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ቻርለስ ሚሸል፤ በሴኔጋል ፕሬዚዳንታዊ ቤተ መንግሥት ከአዲሱ ፕሬዚዳንት ባሲሩ ዲዮማዬ ፋዬ ጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ በሰጡበት ወቅት
የአውሮፓ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ቻርለስ ሚሸል፤ በሴኔጋል ፕሬዚዳንታዊ ቤተ መንግሥት ከአዲሱ ፕሬዚዳንት ባሲሩ ዲዮማዬ ፋዬ ጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ በሰጡበት ወቅት

የሦስት ሀገራት የምዕራብ አፍሪካ ጉብኝታቸውን ትናንት በዳካር የጀመሩት የአውሮፓ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ቻርለስ ሚሸል፤ ስደት እና ልማትን በሚመለከቱ ጉዳዮች ከሴኔጋል ጋራ ‘በቅርበት እንሠራለን’ ሲሉ ቃል ገብተዋል።

ሚሸል በሴኔጋል ፕሬዚዳንታዊ ቤተ መንግሥት ከአዲሱ ፕሬዚዳንት ባሲሩ ዲዮማዬ ፋዬ ጋራ ሆነው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ ኅብረቱ የልማት ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ እና የሕዝቧን ኑሮ ለማሻሻል ሴኔጋል በያዘችው ጥረት ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆኑን ተናግረዋል። አያይዘውም ብዙዎች ያለ ሕጋዊ ሰነድ ለፍልሰት ለሚዳረጉባቸው መንስኤዎች መፍትሄ ፍለጋ ብርቱ ፍላጎት እንዳላቸው ገልፀዋል።

የዓለም ባንክን እና የዓለም የገንዘብ ድርጅትን ጨምሮ በዓለም አቀፍ ተቋማት ውስጥ ይበልጥ አካታች እና ፍትሃዊ አሠራሮች እንዲፈጠሩ የማድረግ አስፈላጊነትን ያነሱት የአውሮፓ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት፣ ይህን እውን ማድረግ የሚያስችሉ አስተዳደራዊ ማሻሻያዎን የሚደግፉ መሆናቸውንም አስታውቀዋል።

ፋዬ አዲሱ የሴኔጋል ፕሬዚዳንት ሆነው የመሪነቱን ሥልጣን ከተቆናጠጡ ወዲህ ሚሸል ምዕራብ አፍሪቃዊቱን ሃገር በመጎብኘት የመጀመሪያው የውጭ ሃገር ባለሥልጣን ሆነዋል።

በሳምንቱ መገባደጅያ ወደ ቤኒን በሚያደርጉት ጉዞ ጉብኝታቸውን የሚያጠናቅቁት ሚሸል በነገው ዕለት ወደ አይቮሪ እንደሚያመሩ ተገልጧል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG