በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአውሮፓ ሕብረቱ ጆሴፍ ቦሬል ኪየቭን ጎበኙ


የአውሮፓ ሕብረት የውጭ ፖሊሲ ኃላፊ ጆሴፍ ቦሬል
የአውሮፓ ሕብረት የውጭ ፖሊሲ ኃላፊ ጆሴፍ ቦሬል

የአውሮፓ ሕብረት የውጭ ፖሊሲ ኃላፊ ጆሴፍ ቦሬል ዛሬ ማክሰኞ ኪየቭን በጎበኙበት ወቅት ሕብረቱ ለዩክሬን በሚሰጠው እና እርሳቸው "የማያወላውል" ባሉት ወታደራዊ እና የገንዘብ ድጋፍ ዙሪያ እንደሚወያዩ ተናግረዋል። ቦሬል ወደ ዩክሬይን ያቀኑት የአውሮፓ ሕብረት ለመጭው አራት ዓመታት ለኪየቭ የመደበውን የ54 ቢሊየን ዶላር ድጋፍ ባጸቀደ ጥቂት ቀናት ውስጥ ነው።

ቦርሬል በኪየቭ ቆይታቸው ዩክሬይን የአውሮፓ ሕብረት አባል ለመሆን በሚያስችሏት ለውጦች ዙሪያ ስለምስትሰራቸው ሥራዎች ከባለስልጣናቱ ጋር የሚነጋገሩ መሆናቸውንም አክለው አመክልክተዋል።

በሌላ ዜና የዓለም አቀፉ አቶሚክ ኢነርጂ ድርጅት (አይኤኢኤ) ኃላፊ ራፋል ግሮሲ የዛፖሪዝሂያ’ን የኑክሌር ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ለመጎብኘት በተያዘ ዕቅድ በዛሬው ዕለት ኪየቭ ገብተዋል።

ግሮሲ ከባለሥልጣናቲ ጋር እንደሚነጋገሩ እና "አሁንም በደካማ አያያዝ ላይ ይገኛል” ያሉትን በሩሲያ ቁጥጥር ስር ባለው የዩክሬን አካባቢ የሚገኘውን የኒዩክሌር ማመንጫ ጣቢያ የደህንነት ሁኔታ የሚገመግሙ መሆናቸውን ተናግረዋል።

በተጨማሪም በጣቢያው ያለው የኒውክሌር ነዳጅ አያያዝ ሁኔታ እንደሚያሳስባቸው፤ በጣቢያው የሚሰሩ ሰራተኞች ቁጥር መቀነሱም ለአይኤኢኤ ሥጋት መደቀኑን ገልጸዋል።

ዛፖሪዝሂያ በአውሮፓ ውስጥ ትልቁ የኒክሌር ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ነው።

በሌላ ዜና ሩስያ በዛሬው ዕለት ሰሜን ምስራቅ ዩክሬን ላይ ያስወነጨፈች ሚሳይል አንድ ሰው ሲገድል ሌሎች ሦስት ሰዎች ማቁሰሉን የዩክሬን ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።

የካርኪቭ አገረ ገዥ ኦሌግ ሲኔጉቦቭ ሲናገሩ ሁለት ‘ኤስ-300’ የተባሉ የሩስያ ሚሳይሎች፡ አንድ ዞሎቺቭ ከተማ ውስጥ የሚገኝ ባለ ሶስት ፎቅ ህንጻ ሆቴል አውድመዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG