በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአውሮፓ ህብረት የኮቪድ-19 ክትባት አነስተኛ ገቢ ላላቸው ሃገሮች ሊለግስ ነው


የህብረቱ ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ዩራሱላ ቮን ደ ሌይን

የአውሮፓ ህብረት 200 ሚሊዮን የኮቪድ-19 የክትባት መድሃኒቶችን አነስተኛ ገቢ ላላቸው አገሮች እስከ መጭው ዓመት አጋማሽ ድረስ ለመስጠት ቃል ገብቷል፡፡

የህብረቱ ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ዩራሱላ ቮን ደ ሌይን ፈረንሣይ ስትራስበርግ ውስጥ ዛሬ በተካሂደው የአውሮፓ ህብረት ዓመታዊ ስብሰባ ላይ አሁን የተገባው ቃል ህብረቱ ከዚህ በፊት ከሰጠው 250 ሚሊዮን የክትባት መድሃኒቶች በተጨማሪ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

በዩናይትድ ስቴትስ ሁሉም የሠራዊቱ አባላት የኮቪድ-19ን ክትባት እንዲወስዱ መታዘዛቸው ተነገረ፡፡ የዩናይትድ ስቴትስ ወታደራዊ ባለሥልጣናት በትናንትናው እለት እንዳስታወቁት እኤአ እስከ ታህሳስ 15 ድረስ የሠራዊቱን የደንብ የለበሰ ሁሉ ክትባቱን እንዲወስድ መታዘዙን አስታውቀዋል፡፡ለተጠባባቂና ለሁሉም የክብር ዘቦች ደግሞ እስከ ሰኔ 30/2022 ድረስ እንዲወስዱ ግዴታ የተጣለባቸው መሆኑን ተመልክቷል፡፡

አስተያየቶችን ይዩ

XS
SM
MD
LG