በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአውሮፓ ኅብረት በሃገራት ላይ ጥሎ የነበረውን ዕገዳ አነሳ


መንገደኞች በባርሴሎና ስፔን የአውሮፕላን ጣቢያ
መንገደኞች በባርሴሎና ስፔን የአውሮፕላን ጣቢያ

የአውሮፓ ኅብረት፣ ከተወሰኑ ሃገራት በሚጓዙ መንገደኞች ላይ ተጥሎ የነበረውን ዕገዳ ትናንት ሲያነሳ አሜሪካውያን ታጓዦች ወደአውሮፓ ሀገሮች ለመግባት ከሚችሉት ዝርዝር ውስጥ አልተካተተም።

የኮሮናቫይረስ መዛመት ከበረታባቸው ሀገሮች ዩናትድ ስቴትስ፣ ብራዚልንና ህንድን ከመሳሰሉት ሃገሮች የሚጓዙት፣ በአሁኑ ወቅት አውሮፓ መግባት አይችሉም ተብሏል።

ቻይና ከአውሮፓ በሚጓዙት ሰዎች ላይ የጣለችውን ዕገዳ ካነሳች፣ ቻይናውያን አውሮፓ መግባት እንደሚችሉ ታውቋል።

የአውሮፓ ህብረት ወደ አውሮፓ ለሚጓዝ በሚችሉትና በማይችሉት መንገደኞች ላይ ውሳኔ የሚሰጠው፣ በየሁለት ሳምንታቱ በሚያደርገው ግምገማ መሰረት ነው።

ኮቪድ-19 ባለፈው ዓመት በቻይና ከተዛመተበት ጊዜ አንስቶ፣ ወደ 10.5 ሚልዮን የሚጠጉ ሰዎች፣ በቫይረሱ ተይዘዋል። የሞቱት ደግሞ 500ሺህ ናቸው።

XS
SM
MD
LG