በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአውሮፓ ሕብረት መሪዎች በፍልሰትኞች ጉዳይ መግባባት ላይ ደረሱ


የአውሮፓ ሕብረት መሪዎች ፍልሰትኞችን በተመለከተ ዛሬ ጠዋት ከአንድ መግባባት ደርሰዋል።

የአውሮፓ ሕብረት መሪዎች ፍልሰትኞችን በተመለከተ ዛሬ ጠዋት ከአንድ መግባባት ደርሰዋል።

የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮ - ከሥምምነት መደረሱ “ጥሩ ዜና ነው” ብለዋል። ሐሙስ ማታ የተጀመረው ንግግር ዛሬ ጎሕ ሲቀድ የተጠናቀቀው “የአውሮፓውያንን ትብብር በማብሰር ነው” ሲሉም አክለዋል።

በሥምምነቱ መሠረት ለመቀበል ፈቃደኞች በሆኑ የሕብረቱ አባል ሀገሮች ውስጥ የፍልሰተኞችና የጥገኝነት አመልካቾች ማዕከል ይቋቋማሉ።

ኢጣልያ ብራሰልስ በተደረገው የአውሮፓ መሪዎች ስብሰባ ላይ ሕብረቱ የሮማውን የስደተኞች ቀውስ ለመፍታት ድጋፉን ሳያስይ - ምንም ዓይነት ሥምምነት ተግባራዊ እንደማታደርግ ማስታውቋ አይዘነጋም።

ኢጣልያ የፍልሰተኞች ማቆያ ማዕከል ስለማስተናገዷ ውሳኔዋን ቆይታ ታሳውቃለች ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሯ ጁሴፔ ኮንቴ አስረድተዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG