በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አውሮፓ እና ቱኒዚያ በበርካታ መስኮች ስምምነት ላይ ደረሱ


የኔዘርላንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ማርክ ሩተ፣ የቱኒዚያ ፕሬዚዳንት ካይስ ሳይድ፣ የአውሮፓ ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ኡርሰላ ቮደር ላየን፣ የጣልያኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ በጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ በሰጡበት ወቅት በካርቴጅ፣ ቱኒዚያ፣ እሑድ እአአ ሐምሌ 16/2023
የኔዘርላንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ማርክ ሩተ፣ የቱኒዚያ ፕሬዚዳንት ካይስ ሳይድ፣ የአውሮፓ ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ኡርሰላ ቮደር ላየን፣ የጣልያኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ በጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ በሰጡበት ወቅት በካርቴጅ፣ ቱኒዚያ፣ እሑድ እአአ ሐምሌ 16/2023

የአውሮፓ ሀገራት መሪዎች እና የቱኒዚያው ፕሬዚዳንት በሚያደርጉት ውይይት፣ የተሻለ ውጤት እያስመዘገቡ እንደኾነ አስታውቀዋል። በኢኮኖሚ እና በንግድ፣ እንዲሁም ለሕይወት አደገኛ በኾነ የሜዲትሬንያን ባሕር ላይ ጉዞ፣ ፍልሰተኞችን በሕገ ወጥ መንገድ ማሻገርን በተመለከቱ ጉዳዮች፣ መግባባት ላይ እንደደረሱ አስታውቀዋል።

የጣልያን፣ የኔዘርላንድ፣ እና የአውሮፓ ኮሚሽን መሪዎች፥ ከአንድ ወር ብዙም ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ቱኒዚያን ጎብኝተዋል። በጉብኝታቸው ወቅት፣ ከቱኒዚያ ጋራ የተፈራረሙት የመግባባቢያ ሰነድ፣ ለአጠቃላይ ትብብር መንገድ ይጠርጋል፤ የሚል ተስፋ እንዳላቸው ተናግረዋል።

መሪዎቹ፣ ባሳለፍነው ሰኔ ቱኒዚያን በጎበኙበት ወቅት፣ የአገሪቱን የተንገዳገደ ኢኮኖሚ ለመደገፍ፣ የድንበር ጥበቃዋን ለማጠናከር እና በተለይም አገሪቱን መነሻ አድርገው ወደ አውሮፓ የሚገቡ ፍልሰተኞችን ለማስቆም የሚውል፣ አንድ ቢሊዮን ዩሮ ቃል ገብተው ነበር።

በዚኽኛው ጉብኝት ግን፣ የአውሮፓ ኮሚሽን ፕሪዚዳንት ኡርሰላ ቮደር ላየን፣ የጣልያኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ እና የኔዘርላንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ማርክ ሩተ፣ ከቱኒዚያው ፕሬዚዳንት ካይስ ሳይድ ጋራ በአደረጉት ውይይት፣ የአውሮፓ ኅብረት ሊሰጥ ስላሰበው የገንዘብ መጠን አልገለጹም።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG