የዓለም አቀፉ የወንጀል ችሎት ዋና ዐቃቤ ሕግ፣ የችሎቱ ዳኞች የሚያንማር ወታደራዊ አገዛዝ መሪ ላይ የእስር ትዕዛዝ እንዲያወጡ ጠይቀዋል። ትዕዛዙ እንዲወጣ የተጠየቀው በሚያንማር በሚገኙ የሮሄንጂያ ሙስሊም ሕዳጣን ማኅበረሰብ ላይ መፈናቀል እና ሰቆቃን ጨምሮ የሰብአዊ ወንጀል ተፈጽሟል በሚል ነው።
እ.አ.አ በ2021 በኦን ሳን ሱ ቺ ላይ መፈንቅለ መንግሥት አካሂደው ሥልጣን የተቆናጠጡት ጀኔራል ሚን ኦንግ ላይንግ፣ በሮሄንጂያ ሙስሊም ሕዳጣን ማኅበረሰብ ላይ መፈናቀል እና ሰቆቃ ፈጽመዋል የሚል ክስ ይቀርብባቸዋል።
ጀኔራሉ፤ አንድ ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች የዘር ማጽዳት ተብሉ ከተገለጸው ዘመቻ ለማምለጥ ወደ ጎረቤት ባንግላዴሽ እንዲሸሹ አስገድደዋል የሚል ክስ ይቀርብባቸዋል። ዘመቻው መጠነ ሰፊ የመድፈር ጥቃት፣ ግድያ እና መኖሪያ ቤቶችን ማቃጠልን የጨመረ ነው ተብሏል።
በባንግላዴሽ በሚገኝ የስደተኞች ካምፕ ሆነው መግለጫ የሰጡት፣ የዓለም አቀፉ ወንጀል ችሎት ዋና ዐቃቤ ሕግ ካሪም ካን፣ በሚያንማር መሪዎች ላይ ተጨማሪ የእስር ትዕዛዞች እንዲወጡ እንደሚጠይቁ አስታውቀዋል።
መድረክ / ፎረም