በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአውሮፓ ኅብረት በግጭት ለተጎዱ የኢትዮጵያ አካባቢዎች የጤና አገልግሎት የሚውል 31 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዩሮ ለገሰ


የአውሮፓ ኅብረት ሎጎ
የአውሮፓ ኅብረት ሎጎ

የአውሮፓ ኅብረት በግጭት በተጎዱ የኢትዮጵያ አካባቢዎች የጤና አገልግሎቶችን እና የጤና ጥበቃ ሥርዓቱን መልሶ ለመገንባት እና ለማጠናከር 31 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዩሮ ወይም 1 ነጥብ ሰባት ቢሊዮን ብር መለገሱን አስታወቀ።

ኅብረቱ ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው በዩኒሴፍ በኩል የሰጠው የገንዘብ ድጋፍ በግጭት በተጎዱ የሀገሪቱ አካባቢዎች ያሉ ሴቶች እና ህጻናትን ህይወት ለማሻሻል የታለመ ነው።

“በጦርነት አሳዛኝ ጉዳት የሚደርሰው በሰዎች ላይ ብቻ ሳይሆን በጤና አገልግሎት ሥርዓቶችም ላይ ጭምር ነው" ያሉት በኢትዮጵያ የአውሮፓ ኅብረት አምባሳደር ሮላንድ ኮቢያ አሁን ሠላም እየተገነባ በመሆኑ ሁሉንም ኢትዮጵያውያን በተሻለ ለመርዳት እንችላለን፣ በተለይም በጤና አውታሮች ውድመት የተነሳ በእጅጉ ተጎድተው የነበሩትን ሴቶች እና ህጻናት" ብለዋል።

በመሆኑም ይህ የገንዘብ ድጋፍ በግጭት አካባቢዎች የጤና አገልግሎቶችን መልሶ ለመገንባት እንደሚውል መግለጫው አውስቷል።

ከዚህም ሌላ በጾታ ተኮር ጥቃቶች ለተጎዱ ሰለባዎች የሚሰጠውን አገልግሎት ለማሻሻል እንደሚውል ተመልክቷል።

የአውሮፓ ኅብረት የሰጠው የገንዘብ ድጋፍ በአፋር፣ በአማራ፣ በኦሮምያ፣በትግራይ እንዲሁም በደቡብ ክልሎች ቁጥራቸው ወደ 2 ሚሊዮን ለሚጠጋ ሴቶች ወንዶች ህጻናት እና ታዳጊዎች እንደሚረዳ ተገልጿል።

XS
SM
MD
LG