በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በፍልሰተኞች ላይ የሚመክር ጉባዔ በማልታ


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

የአምስት የአውሮፓ ህብረት ሀገሮች የአገር አስተዳደር ሚኒስትሮች ከሰሜን አፍሪካ ወደአህጉሪቱ የሚገቡ ጥገኝነት ጠያቂዎችን እንዴት እንደሚከፋፈሉ የሚወስን ሥምምነት ላይ ሊነጋገሩ ማልታ ላይ ተሰባስበዋል።

ፈረንሳይ፣ ጀርመንና ማልታ በፈቃደኝነት ሸክሙን ለመጋራት ያደረጉት ሥምምነት ለሌሎቹም የአውሮፓ መንግሥታት ሸክሙን ከጣሊያን እና ከግሪክ ላይ ለማንሳት አርአያ ይሆናል ብለው የአህጉሪቱ ባለሥልጣናት ተስፋ ያደርጋሉ።

የሀንጋሪ ባለሥልጣናት ግን አራቱ ሃገሮች የደረጉት ሥምምነት ብረሰልስ የፍልሰት ቀውሱ ተባብሶ በነበረባቸው ዓመታት በህብረቱ አባል ሃገሮች ላይ ልትጭን የነበረውን አሰራር በተዘዋዋሪ ሥራ ላይ ለማዋል የታለመ ነው በማለት አንሳተፍበትም ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG