በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አውሮፓ ውስጥ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ እያገረሸ ነው


ፎቶ ፋይል፦ /ሚላን ጣሊያን/
ፎቶ ፋይል፦ /ሚላን ጣሊያን/

ኮሮናቫይረስ አውሮፓ ውስጥም በአዲስ መልክ እያገረሸ ነው። በኢጣልያ በአዲስ መልክ የታየውን፣ የቫይረሱን መዛመት ለመቆጣጠር ሲሉ፣ የሃገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ጁሴፔ ኮንቴ፣ ሦስት ዘርፍ ያላቸው የተለያዩየ የመንቀሳቀስ ዕገዳዎች እንደሚጥሉ አስታውቀዋል።

የሃገሪቱ 20 ክልሎች በቀይ፣ በብርቱካናማና በቢጫ ቀለማት ቀጠና ተከፋፍለው በየደርጃው የመንቀሳቀስ እገዳ እንደሚጣልባቸው ታውቋል። በቀይ ቀለም ያሉት ጥብቅ ዕገዳ እንደሚደረግባቸው፣ በብጫ መስመር ላይ ባሉት ደግሞ፣ ዕግዳው የላላ እንደሚሆን ተገልጿል።

በቀይ ቀለም ሥር በተካለሉት ክልሎች፣ ለሥራና ለህክምና ካልሆነ በስተቀር፣ ከቤታቸው እንዲወጡ አይፈቀድም። በብርቱካናማ ወይም በመካከለኛ ደረጃ በተመደቡት ክልሎች፣ በከተሞቻቸው አካባቢ እንደልብ መንቀሳቀስ ይችላሉ። ይሁንና ወደሌሎች ስፍራዎች መዘዋወር አይችሉም። ምግብ ቤቶችና ቡና ቤቶች፣ ገዝቶ ለመሄድ ብቻ እንጂ አዛው መስተናገድ አይቻልም። በመላ ሃገሪቱ ከምሽቱ 4፡00 ሰአት እስከ ንጋቱ 11፡00 ሰአት፣ የሰዓት እላፊ ገደብ ይደንገጋል። አዲሱ ዕገዳ ከነገ አንስቶ ለ27 ቀናት እንደሚዘልቅ ታውቋል። በተያያዘም ብሪታንያ፣ ጀርመንና ቤልጂምም በአዲስ መልክ የተከተሰውን የቫይረሱን መዛመት ለመቀነስ ሲሉ፣ ጥብቅ የመንቀሳቀስ ዕገዳ ደንግገዋል።

የዴንማርክ ጠቅላይ ሚኒስትር መቲ ፍሬድሪክሰን የኮሮናቫይረሱን እንዳይዛመት በመስጋት፣ በሀገሪቱ ያሉትን፣ 15ሚሊዮን “ሚንክ” የሚባሉ እንስሳትን ለማጥፋት መወሰኑን አስታውቀዋል።

ዴንማርክ በዓለም በብዛት የሚንክ ቆዳ ተረፈ ምርት ከሚያቀርቡት ሀገሮች አንዷ መሆናን ይታወቃል።

XS
SM
MD
LG