በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ወደ አውሮፓ ኅብረት የሚደርገው ፍልሰት 10 በመቶ ጨምሯል ተባለ


ፎቶ ፋይል፦ የአፍሪካ ፍልሰተኞች የሜዲትሬንያን ባህር አቋርጠው ወደ አውሮፖ በጀልባ ተጭነው ሲጓዙ
ፎቶ ፋይል፦ የአፍሪካ ፍልሰተኞች የሜዲትሬንያን ባህር አቋርጠው ወደ አውሮፖ በጀልባ ተጭነው ሲጓዙ

በያዝነው የፈረንጆች ዓመት የመጀመሪያ አጋማሽ ላይ ወደ አውሮፓ ኅብረት ሀገራት የሚደረግ ሕገ ወጥ ፍልሰት በ 10 በመቶ እንደጨመረ የኅብረቱ የድንበር ባለሥልጣን ዛሬ አስታውቋል።

በሜዲትሬንያን ባህር በኩል የሚደርገው ፍልሰት ከፍተኛውን ቁጥር እንደሚይዝ ‘ፍሮንቴክስ’ የተሰኘው የኅብረቱ የድንበር ባለሥልጣን አስታውቋል።

ባልተለመዱ የድንበር መሻገሪያዎች በኩል ከ132ሺሕ በላይ ፍልሰተኞች ወደ አውሮፓ ኅብረት ለመሻገር መሞከራችውን ባለሥልጣኑ አስታውቆ፣ ባለፈው ዓመት ከነበረው ጋር ሲነጻጸር የ10 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል ብሏል።

ግማሽ የሚሆኑት ፍልሰተኞች በቱኒዚያ በኩል ወደ ጣሊያን የገቡ ሲሆኑ፣ ይህም አጠቃላይ ፍልሰቱን በአንድ ሦስተኛ እንዲጨምር አድርጓል ተብሏል።

ፍልሰቱን ለመከላከል በሚል ኅብረቱ በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ ከቱኒዚያ ጋር ስምምነት የተፈራረመ ሲሆን፣ ከመካከለኛው ምሥራቅ፣ አፍሪካ እና እሲያ የሚመጡትን ፍልሰተኞች ለማስቆም ከየሃገራቱ መንግታት ጋር ኅብረቱ የሚያደርገው ትብብር ዲሞክራሲያዊ ያልሆኑ መንግስታትን ያበረታታል ሲሉ የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች ነቀፌታ ያሰማሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG