በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኤርትራ የልዑካን ቡድን ወደ አዲስ አበባ ልትልክ ነው


የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ
የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ

የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ መፍትሔ ታጥቶለት ሳይገኝለት ዓመታት ለዘለቀው የሁለቱ ሀገሮች የድንበር ውዝግብ ሁነኛ መፍትኄ ተስፋ ባንሰራራ በተባለ ውሳኔያቸው አንድ የልዑካን ቡድን ወደ አዲስ አበባ ሊልኩ ማቀዳቸውን ይፋ አደረጉ።

የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ መፍትሔ ታጥቶለት ሳይገኝለት ዓመታት ለዘለቀው የሁለቱ ሀገሮች የድንበር ውዝግብ ሁነኛ መፍትኄ ተስፋ ባንሰራራ በተባለ ውሳኔያቸው አንድ የልዑካን ቡድን ወደ አዲስ አበባ ሊልኩ ማቀዳቸውን ይፋ አደረጉ።

ፕሬዚዳንቱ ይህን ያስታወቁት በዛሬው ዕለት በዋና ከተማይቱ አስመራ የሰማዕታትን ቀን ለማክበር በተሰናዳ ሥነ ሥርዓት ባሰሙትና ደም ላፋሰሰው የሁለቱ አገሮች ግጭት “አቅጣጫ ለዋጭ” ያሉትን የኢትዮጵያን የሰላም ጥረት በገለጹበት ንግግራቸው ነው።

የሰባ ሁለት ዓመቱ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አክለውም፣ የልዑካን ቡድኑን ወደ አዲኣስ አበባ ለመላክ የወሰኑት የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አሕመድ የያዙትን አቋም በቅጡ ለመረዳትና ብሎም “ቀጣዩን ዕቅድ ለመንደፍ” መሆኑን ተናገረዋል።

ይሄም እአአ ከ1998 እስከ 2000 በሁለቱ ተጎራባች አገሮች መካከል ለተካሄደው ጦርነት እልባት ለማበጀት ታልሞ በጊዜው የተደረሰውንና እስካሁን ግን ተፈፃሚነት ሳያገኝ የቆየ የሰላም ስምምነት ሙሉ በሙሉ የሚያከብሩ መሆናቸውን የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚንስትር አብይ የሰጡትን አስደማሚ ቃል አስመልክቶ በፈላጭ ቆራጭነትና ራሷን ከተቀረው ዓለም በመነጠል በአሕጉሪቱ ከቀዳሚዎቹ ተርታ የምትሰለፈው ኤርትራ ለመጀመሪያ ጊዜ የሰጠችው ምላሽ መሆኑ ነው።

ኤርትራ የልዑካን ቡድን ወደ አዲስ አበባ ልትልክ ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:21 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG