በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"በየቀኑ ሰዎች እየተገደሉ ነው"- የባቢሌ ከተማ ነዋሪ


“በሶማሌ ክልል ልዩ ፖሊስና ሚሊሺያዎች አማካኝነት የሚደርሱ ጥቃቶች አሁንም አልተቋረጡም ” ሲሉ ነዋሪዎች አማረሩ

"በየቀኑ ሰዎች እየተገደሉ ነው"- የባቢሌ ከተማ ነዋሪ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:48 0:00

በኦሮሚያና በሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ ድንበሮች ላይ በሚገኙ ከተሞች የሚኖሩ ነዋሪዎች፤ “በሶማሌ ክልል ልዩ ፖሊስና ሚሊሺያዎች አማካኝነት የሚደርሱ ጥቃቶች አሁንም አልተቋረጡም በየቀኑ ሰዎች እየተገደሉ ነው” ሲሉ አማረሩ።

በምስራቅ ሐረርጌ ባቢሌ ከተማ በዚህ ሣምንት ብቻ አራት ሰው እንደሞተ ገለፀው እንደ ጤና ጣቢያና ትምሕርት ቤት ያሉ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በተወሰኑ ቀበሌዎች ውስጥ መዘጋታቸውን ጠቁመዋል።

በሞያሌ የሚገኙ ነዋሪዎችም በበኩላቸው በየቀኑ የአካል ጥቃት እንደሚደርስና ግጭቱ የሰዎችን የዕለት ተዕለት ግንኙነት በማበላሸቱ በከተማ ውስጥ ለብቻ መንቀሳቀስ አስፈሪ መሆኑ ተናግረዋል።

በዚህ ጉዳይ ላይ ማብራሪያ ለማግኘት የኦሮሚያም ሆነ የሶማሌ ክልል ባለሥልጣናትን ለማግኘት አልቻልንም።

የከተማዎቹ የቀበሌ መስተዳድር ኃላፊዎች ግን ሁኔታው አሁን ካለው የከፋ መልክ ሳይዝ አፋጣኝ መፍትሔ ሊፈለግለት ይገባል ሲሉ ያስጠነቅቃሉ።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG