በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያ ማሣዎችና ችግሮቻቸው


ፀረ-ሰብል ተኀዋስያን፣ በሽታዎችና ዐረሞች በኢትዮጵያ ማሣዎች ላይ በየአዝመራው ከባድ ጉዳት ያደርሣሉ፡፡

ይህ ችግር ደግሞ እንዲሁም በድርቆችና ኋላቀር በሆነው ባሕላዊ የአስተራረስ ዘዴ፣ አነስተኛና የተናጠል በሆነውም ግብርና ምክንያት የተዳከመውን የምግብ ዋስትና ይበልጥ እያዳከመው ያለ ችግር ነው፡፡

በዚህ ርዕስ ላይ በጀመርነው ተከታታይ ዘገባ የፕሮግራሙ አዘጋጅና አቅራቢ ሰሎሞን አባተ ያነጋገራቸው ባለሙያ ዶ/ር በዳዳ ግርማ ገበሬው ልዩ ትኩረት ሊሰጣቸውና ችግሮቹን ለመቆጣጠር ከአካባቢ አካባቢ ሊወራረሷቸው ስለሚገቡ የመከላከያ ዘዴዎች ይናገራሉ፡፡

የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ባለሙያውና ዋግን የመቆጣጠር ዓለምአቀፍ ጥረት የኢትዮጵያ ፕሮግራም አስተባባሪ የሆኑት ዶ/ር በዳዳ በቅርቡ ከእንግሊዝ መንግሥትና ከቢልና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን የተገኘ አርባ ሚሊዮን ዶላር በተለያዩ ሃገሮች ውስጥ ለሚገኙ 15 የምርምርና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ድጋፍ እንደሚውል ይናገራሉ፡፡

ለዝርዝሩ ቃለ ምልልሱን ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG