አዲስ አበባ —
ላልተወሰነ ጊዜ ቆሞ የነበረው ወደ አረብ ሃገሮች የሚደረገው የሥራ ጉዞ በመጭው ዓመት የመጀመሪያ ወራት እንደሚከፈት የሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
አሠራሩ እንደቀድሞ እንደማይሆን የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ቃል አቀባይ አቶ ግርማ ሸለመ ገልፀዋል፡፡
ወደውጭ የሚሄዱት ኢትዮጵያዊያን በቅድሚያ ሥልጠና ማግኘት እንደሚኖርባቸውና የቅድመ-ጉዞ ገለፃ እንደሚሰጣቸው የተናገሩት አቶ ግርማ ሥልጠናው የሚሰጠው ለውጭ ጉዞ ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያ ውስጥም ባሉት የሥራ ዕድሎች የተሻሉ ተወዳዳሪዎች እንዲሆኑ ለማድረግ መሆኑን አክለው አመልክተዋል፡፡
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡