በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የባለሥልጣናቱ መግለጫ የመለስን ሕመም ክብደት ያሣያል


የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት ዛሬ የሰጡት መግለጫ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ህመም ከባድ መሆኑን ይጠቁማል ሲሉ ቀደሞ በኢትዮጵያ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ዴቪድ ሺን አስታወቁ፡፡

(ይህ ገፅ ሲከፈት የተደራረቡ ወይም የተረበሹ ድምፆችን የሚሰሙ ከሆነ ኮምፕዩተርዎ ከአንድ በላይ ድምፅ ማጫወቻ አለው ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ከዚህ ፅሁፍ ሥር ካሉት ማጫወቻዎች አንደኛውን ብቻ አስቀርተው ሌሎቹን ያቁሟቸው፡፡)

ዴቪድ ሺን አሁን ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው የጆርጅ ዋሽንግተን ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሣይንስ ፕሮፌሰር ናቸው፡፡

የኢትዮጵያ የመንግሥት ኮምዩኒኬሽንስ መሥሪያ ቤት ባለሥልጣናት ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ሃኪም ረዘም ያለ የህመም ፈቃድ እንዲወስዱ መክረዋቸዋል፥ ሲሻላቸዉ ወደ ሥራ ይመለሣሉ ማለታቸው የጤና ችግሩ ከባድ መሆኑን ያመለክታል፤ ህመሙ ከባድ ባይሆን ኖሮ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ሥራ የሚመለሱበትን ቁርጥ ያለ ቀን ያሣውቁ ነበር ብለዋል ሺን፡፡

አምባሳደር ዴቪድ ሺን ከጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ መንግሥት ጋር ለረጅም ጊዜ በቅርበት የሠሩ በመሆናቸው በዚህ ትኩረት በሚስብ ጊዜ ውስጥ ውስጡን በመንግሥት ውስጥ ምን እንደሚካሄድ ግምታቸውን ሲጠየቁ ባለፈው ግንቦት ለሃያዎቹ ከበርቴ ሃገሮች ጉባዔ ዋሽንግተን ዲ.ሲ. በተገኙበት ጊዜ ከሌሎች ሰዎች ጋር ሆነው እንዳገኙዋቸውና ያኔ ምንም የጤና መቃወስ ምልክት እንዳላዩባቸው፣ ይልቁንስ በጣም ጤናማ ይመስሉ እንደነበረ ጠቁመዋል።

ነገር ግን አቶ መለስ አሁን መወያያ ለሆነው የጤናቸው ጉዳይ ፍንጭ የሚሰጡ አንድ ሁለት አስተያየቶች ጣል አድርገው ነበር ብለዋል።

ከዚያ አስተያየታቸው እንደተረዱትም ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ስለህመማቸው አስቀድመው ሳያውቁ እንዳልቀሩና ተተኪ መንግሥት አቅደዋል የሚል ግምታቸውን አጋርተዋል።

ዝርዝሩን ከዘገባው ያድምጡ።

(ገፁ ሲከፈት የተደራረቡ ወይም የተረበሹ ድምፆችን የሚሰሙ ከሆነ ከዚህ ሥር ካሉት ማጫወቻዎች አንደኛውን ብቻ አስቀርተው ሌሎቹን ያቁሟቸውና የሚጫወተውን እንደገና ያስጀምሩት፡፡ )


XS
SM
MD
LG