አዲስ አበባ —
በነ አቶ መላኩ ፋንታና በሌሎች ሁለት መዝገቦች የሙስና ክሥ ተመሥርቶባቸው ጉዳያቸው ለዛሬ ለብይን ተቀጥሮ የነበረ ተከሣሾች ጉዳይ ለሣምንት፤ ጥቅምት 15/2008 ዓ.ም ተቀጥሯል፡፡
የከፍተኛው ፍርድ ቤት 15ኛ ወንጀል ችሎት ጉዳዩን የቀጠረው ከሕገመንግሥት አጣሪ ኮሚሺን ውሣኔ በኋላ ብይኑ አልደረሰልንም በሚል እንደሆነ ታውቋል፡፡
ክሡ ከተመሠረተ በኋላ አዲስ የጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 859 በ2006 ዓ.ም በመውጣቱና በአዋጁ መሠረት ከወንጀልነት ወደ አስተዳደራዊ ጉዳይነት የተለወጡ አንቀፆች በመኖራቸው ለሕገመንግሥት ትርጓሜ ወደ አጣሪ ኮሚሺን ተልኮ እንደነበር ተገልጿል፡፡
የአጣሪ ኮሚሺኑ መልስ የተገኘ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ ብይኑ እንዳልደረሰለት በመግለፅ ለሣምንት ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
ለተጨማሪ ከላይ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
የጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 859/2006ን የያዘውን ፌደራል ነጋሪት ጋዜጣ ሙሉ የፒዲኤፍ ቅጅ ለማግኘት ከታች ያለውን ማገናኛ ተጭነው ይከተሉ፡፡
http://www.erca.gov.et/images/Documents/Customs/Proclamations/Proclamation_859.pdf