በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮ-ቴሌኮምና የደንበኞቹ ቅሬታዎች


የደንበኞችን እርካታ ከመፍጠር አንፃር ባለፉት ስድስት ወራት የተሣካ ሥራ ማከናወኑን ኢትዮ-ቴሌኮም አስታውቋል። ቪኦኤ ካነጋገራቸው ደንበኞች አብዛኞቹ ግን ለውጦች ቢኖሩም የጥራት ችግር በዚያው ልክ መጨመሩን ገልፀዋል።

ከጥራት አንፃር ችግሮች መኖራቸውን የተቀበሉት የኮምዩኒኬሽን፣ ኢንፎርሜሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ግን ለውጦች መኖራቸውን አስረድተዋል።

የቀድሞውን የኢትዮጵያ ቴሌኮምዩኒኬሽንስ ኮርፖሬሽን በመተካት በኅዳር 2010 (እአአ) የተቋቋመው ኢትዮ-ቴሌኮም ኃላፊዎች ትናንት ሸራተን አዲስ ውስጥ በሰጡት መግለጫ ስኬት ባሏቸው ነጥቦች ላይ ነው ያተኮሩት፡፡

በ2010 ዓ.ም. 6.6 ሚሊየን የነበረው የሞባይል ተጠቃሚ ቁጥር 15 ሚሊየን መድረሱ፣ ከሐምሌ እስከ ታኅሣስ ባሉት ስድስት ወራት ብቻ 5.6 ቢሊየን ብር ገቢ መገኘቱ በኃላፊዎቹ ከተጠቀሱት ነጥቦች መካከል ናቸው፡፡ አዲስ የሲም እና የመጠቀሚያ ካርድ ሥርጭት ስትራተጂ ተግባራዊ መደረጉም ተወስቷል፡፡

ድርጅቱ በተለይ የሞባይል ስልክን በተመለከተ ሌሎችም ተጨማሪ አገልግሎቶችን መስጠት መጀመሩን ኃላፊዎቹ አብራርተዋል፡፡

ከአሠራር አንፃር የተደረጉ ሌሎች ለውጦችና የአገልግሎቶች ዓይነቶችም በመግለጫው ተዘርዝረዋል፡፡

ይህ መግለጫ ግን በተለይ በቅርብ ጊዜ እየተደመጡ ካሉ የደንበኞች ቅሬታዎች አንፃር በትክክለኛ ጊዜ የመጣ አይመስልም፡፡ የሞባይልም ሆነ የኢንተርኔት አገልግሎት ለማግኘት ኢትዮ-ቴሌኮም በተለያየ ዋጋ የሚያሠራጫቸውን ካርዶች መግዛት ቢያስፈልግም በተለይ ካለፈው አንድ ወር ወዲህ የተገዙትን ካርዶች መሙላት እያስቸገራቸው እንደሆነ በርካታ ደንበኞች ያማርራሉ፡፡

እነዚህደንበኞች እንደሚሉት ካርዶቹ የሚሞሉት ሰዓታት አንዳንዴም ቀናት ዘግይተው ነው፡፡ ጭራሽ የማይገባበት አጋጣሚም ይፈጠራል፡፡

የእስክንድር ፍሬውን ዘገባ ያዳምጡ።

XS
SM
MD
LG