በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአውሮፓ ሕብረት ሪፖርት ላይ የ"ራዕይ" ዕይታ


"የአውሮፓ ሕብረት ታዛቢ ቡድን ሪፖርት 'እንዳያማህ ጥራው፤ እንዳይበላ ግፋው' አካሄድ ታይቶበታል" ሲል የኢትዮጵያ ራዕይ ፓርቲ አስታወቀ።

ሪፖርቱ በአዲስ አበባ እንዳይቀርብ መንግሥት ስለመከልከሉም፣ ቡድኑ በቂ መረጃ አላቀረበም ብሏል።

ከወራት መዘግየት በኋላ ብራስልስ ውስጥ ይፋ የተደረገው የአውሮፓ ሕብረት የማጠቃለያ ሪፖርት በመንግሥትም ሆነ በተቃዋሚዎች በኩል የተለያየ አስተያየት እየተሰጠበት ነው፡፡

በ2002ቱ ምርጫ ከተሣተፉት አንዱ የኢትዮጵያ ራዕይ ፓርቲ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ሪፖርቱ መዘግየቱንና ግልፅነትም እንደሚጎድለው አስታውቋል፡፡ ፓርቲው የቡድኑን ሪፖርት በጥቅሉ የማጣጣል ወይም የማወደስ መስመር እንደማይከተልም ገልጿል፡፡

እጅግ ዘግይቶ መቅረቡንና ይዘቱም 'እንዳያማህ ጥራው፤ እንዳይበላ ግፋው' ዓይነት መሆኑን ነው የኢትዮጵያ ራዕይ ፓርቲ ጠቁሟል፡፡

የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው አቶ ተሻለ ሰብሮ ሪፖርቱ "የፖለቲካና የአቋም ወኔ ያነሰውና ወላዋይነትም የታየበት ነው" ብለዋል፡፡

ለዝርዝሩ ዘገባውን ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG