አዲስ አበባ —
ኢትዮጵያ “ሰላማዊ ነች፤ ተቋማቷም ሥራቸውን ያለምንም ችግር እያከናወኑ ናቸው” ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ወርቅነህ ገበየሁ ለውጭ ሃገሮች ዲፕሎማቶች ተናግረዋል።
የአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር አሿሿምም “በጣም በተሳለጠ ሁኔታ እየተካሄደ” መሆኑን ዶ/ር ወርቅነህ ጠቁመዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ባደረጉት ገለፃ ላይ የተገኙ ተቀማጭነታቸው አዲስ አበባ የሆነ አምባሣደሮች እና ዲፕሎማቶች ግን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ለመፍትኄ እርምጃዎች እንቅፋት እንዳይሆንና ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች እንዳይጣሱ ሥጋታቸውን ገልፀዋል።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ