ዋሺንግተን ዲሲ —
በኬንያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ እንዳለው ኢትዮጵያውያኑ ወደ ሀገራቸው የሚመለሱትም ኤምባሲው ከሚመለከታቸው የማላዊ መንግሥት ባለሥልጣናት ጋር ተነጋግሮ በተደረሰው ሥምምነት መሠረት ነው፡፡
በተያያዘ ዜና በህገ ወጥ መንገድ ወደ ኬንያ ለመግባት ሲሞክሩ ተይዘው በኬንያ እስር ቤት ውስጥ የሚገኙ 42 ኢትዮጵያውያን እንደሚመለሱ ተገልጿል፡፡ በቅርቡም በተመሳሳይ ሁኔታ ተይዘው የነበሩ 103 ኢትዮጵያውያን መመለሳቸው ይታወሳል።
በሌላ በኩል በታንዛኒያ ማረሚያ ቤት ውስጥ ለሦስት ዓመታት ታስረው የነበሩ 34 ኢትዮጵያውያን ተለቀዋል። ወደሃገራቸው ለመመለስ ዝግጅቱ እስኪጠናቀቅ ዋና ከተማዋ ወደ ሚገኘው እስር ቤት መዘዋወራቸውን ተገልጿል።
በዚያ ያለው የኢትዮጵያ ኤምባሲ መናገሩን ያገር ውስጥ ምንጮች አመልክተዋል፡፡
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ