በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያውያን የተቃውሞ ሰልፍ በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ደጃፍ፤


ተቃውሞ:- በኢትዮጵያ ጋዜጠኞች፥ የኢንተርኔት አምደኞች፥ የፖለቲካ መሪዎኞችና ሌሎች ዜጎች ጉዳይና የአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ ዘገባዎች፤

የኢትዮጵያውያን የተቃውሞ ሰልፍ በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ደጃፍ፤
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:56 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ


ኢትዮጵያውንና ኢትዮጵያውያን አሜሪካውያን በዛሬው እለት በዋሽንግተን ዲሲው የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ደጃፍ የተቃውሞ ሰልፍ አካሂደዋል።

በኢትዮጵያ የታሰሩ ተቃዋሚ መሪዎችን፥ የጋዜጠኞችንና የድረ ገጽ አምደኞችን እስር በመቃወም የተሰለፉት ኢትዮጵያውያን “የተዛባ ዜና አሰራጭቷል፤” ያሉትን የአሜሪካ ድምጽ ራዲዮን የዜና ዘገባም ተችተዋል።

በቅርቡ በአውሮፕላን ጉዞ ላይ ሳሉ፤ ለቆይታ ካረፉባት ሰንዓ አውሮፕላን ማረፊያ በየመን መንግስት ተይዘው ለኢትዮጵያ መንግስት የተሰጡትን የተቃዋሚው የግንቦት ሰባት ፖለቲካ ፓርቲ ዋና ጸሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን እስር ጨምሮ፤ በአገር ውስጥ የተቃዋሚ መሪዎችንና የጋዜጠኞችን እስር በመቃወም አደባባይ የወጡት ሰልፈኞች፤ “ዩናይትድ ስቴትስ በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብትና የሕግ የበላይነት ከበሬታ ትኩረት መስጠት አለባት፤” ሲሉ ጥሪ አሰምተዋል።

ለውጭ ጉዳይ ሚንስትር ጆን ኬሪ በቀጥታ ባሰሙቡት ጥሪም “አምባገነኑን የኢትዮጵያን መንግስት፤” መደገፍ ያቁሙ ሲሉ ጠይቀዋል።

ሰልፈኞቹ በውጭ ጉዳይ ሚንስትር ላስተጋቧቸው ሃሳቦች አክብሮት እንዳለው የገለጸው የአሜሪካ ድምጽ በበኩሉ፤ ሁሉም የአሜሪካ ድምጽ አገልግሎቶች ለሚዘግቡት ዘገባ ትክክለኝነት የሚሰጡትን ልዩ ትኩረት አመልክቶ ትክክለኛና ሚዛናዊ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚደረጉ ጥረቶች አንዳንድ ጊዜ ከተለያዩ ክፍሎች ቅሬታ እንደሚቀርባቸው ገልጿል።

የአሜሪካ ድምጽ በሚያቀርበው ዜናና መረጃ ትክክለኝነትና ሚዛናዊነት ላይ እምነታችሁን ያሳደራችሁ አድማጮቻችንን እያመሰገን በየዕለቱ በምናቀርባቸው ዘገባዎችም እምነታችሁን ለመግዛት እንጥራለን፤ ሲል ቋጭቷል።

XS
SM
MD
LG