በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በማልታ እስር ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች የድረሱልን ጥሪ አሰሙ


የሚበዙት ወጣቶች ፥ ታዳጊዎች እና ህጻናትም አሉባቸው

በመቶዎች የተቆጠሩ ኢትዮጲያውያን እና ስደተኞች ከወራት በፊት ከሊቢያው የርስ በርስ ጦርነት በባህር አደገኛ ጉዞ ተንጠላጥለው የተወሰኑት ህይወታቸውን ሲያጡ ገሚሱ በህይወት ማልታ መሬት ላይ ደርሰዋል

የሚበዙት ወጣቶች ፥ ታዳጊዎች እና ህጻናትም አሉባቸው።

የማልታ መንግሥት አገሬ በህገወጥ መንገድ የገባችሁ ናችሁ ብሎ እስር ቤት አጉሮ የተለያዩ ሀገሮች ዜጎች የሆኑት ፥ ኤርትራውያን ፥ ሱዳናውያን ወዘተ ጉዳያቸው መንገድ እየያዘ ሲለቀቁ አሁንም በእስር ላይ ያሉ ብዙዎች አሉ።

በተለያየ በሽታ ታመው የሚሰቃዩ ፥ ተገቢውን ህክምናም እንደማያገኙ ስደተኞቹ ይናገራሉ ።

በከባድ ህመም በመሰቃየት ላይ የምተገኘው አንዱዋ የሃያ አራት ዓመትዋ ሳሚራ አብዱ አንዱዋ ነች።

ለአዲሲቱ ኢትዮጲያ የጋራ ንቅናቄ የተባለው ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ኦባንግ ሜቶ የስደተኞቹን ጉዳይ በመከታተል የማልታ መንግሥት መብታቸውን እንዲያከብር በማሳሰብ ደብዳቤ ጽፈዋል ።

ሁለቱንም አነጋግረናል ያድምጡ።

ተመሳሳይ ርእስ

XS
SM
MD
LG