የአፍሪካ ማኅበረሰቦች በህብረት የሚገኙበት፣ የማኅበረሰብ አባሎቻቸውን መብትና ነፃነት ለማስከበር፣ በሥራ ገበታቸውም ላይ የሚገጥማቸውን የመብት ጥሰት ለመከላከል የሚሠራ መንግሥታዊ ያልሆነ ስብስብ ባለፈው ቅዳሜ ዋሽንግተን አካባቢ ባሉ አውሮፕላን ጣቢያዎች የሚሰሩ ኢትዮጵያውያን ላነሷቸው ጥያቄዎች ስለተገኙት ድሎች ለኢትዮጵያውያን ማኀበረሰብ መሪዎች አስረድቷል።
ዋሽንግተን ዲሲ አካባቢ በሬገንና በዳላስ አውሮፕላን ጣቢያዎች የሚገኙ ሠራተኞች፣ ለብዙ ጊዜ ሲያቀርቡ የነበረውን የደምወዝ ጭማሬና የመብት መከበር ጥያቄ፣ ካለፈው ጥር ወዲህ ከግብ ማድረሱን ገልጿል።
ይህ ድል የተገኘውም፣ ዋሽንግተን ዲሲ አካባቢ በሚገኙ የሠራተኞች ማኅበራትና በኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ መሪዎች የተባበረ ትግል እንደሆነ ተገልጿል።
ለመሆኑ ምን ምን ድሎች ተገኙ? የስብሰባው አዘጋጅስ ማነው?
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ