የምግብ ቤቱ ባለቤት ደረጀ ከኢትዮጵያውያ ከወጣ 20 አመት በላይ ሆኖታል፡፡ ቤተሰቦቹ በሙሉ በዋሽንግተን ዲሲ ከተማ ይኖሩ ስለነበር፤ በፊት ከሚኖርበት ካናዳ ወደ ዋሽንግተን ዲሲ መጥቶ ኑሮውን በዋሽንግተን ዲሲ ይቀጥላል፡፡ ወንድምና እህቶቹ፤ ብዙዎቹ በምግብ ቤት ስራ ላይ ስለሚገኙ፤ ደረጀም የግሉ የሆነ ምግብ ቤት ሊከፍት ይነሳሳል፡፡ ምግብ ቤቱን ከሌሎች የኢትዮጵያ ምግብ ቤቶች ለምን ለየት ለማድረግ እንዳሰበ ምሳ ሰዓት ላይ ለጎበኘችው ልደት አበበ አጫውቷታል፡፡
ደረጀ የምግብ ቤት ባለቤትና የፎቶግራፍ ባለሙያም ነው፡፡ እወደዋለሁ ለሚለው የፎቶ አንሺነት ሙያ ብዙ እርቆ መሄድ አያስፈልግም፡፡ ምግብ ቤቱ ፊት ለፊት አስፋልቱን ተሻግሮ ፎቶ ቤቱ ይገኛል፡፡ የሚበዙት ደንበኞቹ በሰርግ ፎቶግራፍ ስራ ነው የሚያውቁኝ ይላል ደረጀ፡፡
ለዝርዝሩ ዘገባውን ያድምጡ፡፡