የአዲስ አበባውን ማስተር ፕላን እቅድ በመቃወም ለሰላማዊ ሰልፍ በወጡ የኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያን ላይ በመንግሥት ኃይሎች ተፈጽሟል፤ ያሉትን ግድያ፥ ድብደባና እሥራት በመቃወም፥ እዚህ በዋሺንግተን ዲሲና አካባቢዋ የሚኖሩ የኦሮሞ ማህበረሰብ አባላት፥ ካለፈው ረቡዕ ጀምሮ ለሦሥት ቀናት የዘለቀ የረሃብ አድማ አድርገዋል።
“መንግሥት በዜጐቹ ላይ እያደረሰ ያለው ችግር ተባብሶ ቀጥሏል፤” የሚሉት በWhite House ቤተ መንግሥት ፊት ለፊት ለሦስት ቀናት በረሃብ አድማው የተሳተፉ ሰላሳ የሚጠጉ ሰዎች፥ ዓላማቸው ሁኔታውን ለአሜሪካና ለዓለም ሕዝብ ለማሳወቅ መሆኑን ይናገራሉ። ለዝርዝሩ ዘገባውን ያድምጡ።