በዚህ ሰሞኑን በፀደቀው አዲስ ሕግ መሠረት የከተማ መሬት መያዝ የሚቻለው በሊዝ ማለትም በኪራይ ብቻ ነው።
ከዚህ ቀደም የመሬት ይዞታ የነበራቸውና መኖሪያ ቤት የሠሩ ሁሉም ወደዚሁ ሥርዓት እንዲገቡና የቦታ ኪራይ እንዲከፍሉ ይጠይቃል።
አንድ አንጋፋ የሕግ ባለሙያ ለቪኦኤ እንደገለጹት ይህ አዋጅ ከ1967ቱ የከተማ ቦታና ትርፍ ቤት አዋጅ በመቀጠል የወጣ ሥር ነቀል የመሬት አዋጅ ነው።
የሕግ ባለሙያውን አቶ አብዱ ዓሊ ሒጂራን ያነጋገረውን የእስክንድር ፍሬውን ዘገባ ያዳምጡ።