አዲስ አበባ —
ከሞት ጋር በቅርብ ርቀት ስንተያይ ከኖርንባት ሃገር ወደ ትውልድ ሥፍራችን መምጣታችን አስደስቶናል ሲሉ ትናንት አዲስ አበባ የገቡ ከየመን ተመላሾች ኢትዮጵያዊያን አስታውቀዋል፡፡
መንግሥት ለዚህ መሣካት ያደረገውን ጥረትም አወድሰዋል፡፡
ወደ ሃገራቸው ለመመለስ አራት ሺህ ኢትዮጵያዊያን እስከአሁን ከ2500 በላይ መግባታቸውን የገለፁት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ቀሪዎቹንም ከአንድ ሣምንት ባነሰ ጊዜ ማጓጓዝ እንደሚቻል ጠቁመዋል፡፡
ለዝርዝሩ የእስክንድር ፍሬውን ዘገባ የያዘውን የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡