ሊቢያ ውስጥ በተቃውሞውና በግጭቱ ውስጥ የተጠመዱት ኢትዮጳውያን ስደተኞች በዓለም ዙሪያ ለሚገኙ ወገኖቻቸው የድረሱልን ጥሪ እያሰሙ ናቸው።
በዚህ በዋሽንግተን ዲሲና መካባቢዋ የሚንቀሳቀሰው የኢትዮጲያ ሴቶች የሰላምና የልማት ድርጅት ተጠሪ ወይዘሪት ወሰንየለሽ ደበላ ቢያንስ ለዓለም ጩኸታችንን ማሰማት ይቻለናል ብለዋል ፥ ሁሉም በያለበት ይህንኑ እንዲያደርግም ተማጽኖ አቅርበዋል።
በተለይ በዓለም ዙሪያ ያሉ ህዝዛዊ ማህበራት ሬዲዮ ጣቢያዎች፥ የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች በሙሉ ድምጻቸውን እንዲያሰሙ ጥሪያችን አቅርበዋል።