ዋሽንግተን ዲሲ —
በኢትዮጵያ የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ከታወጀ በኋላ የታሰሩ ከ11 ሺህ በላይ እስረኞች በተለያዩ ቦታዎች በሁለተኛ ዙር "የተሃድሶ ስልጠና" ወስደው መለቀቃቸው ተገልጿል። ከእነዚህ ውስጥ የበዛውን ቁጥር የሚይዙት በጦላይ የማቆያ ማእከል ስልጠና የወሰዱት እንደሆኑም የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጁ ኮማንድ ሴክረትሪያት በጥር ወር መጨረሻ ለሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ማስታወቁ ይታወሳል።
ጽዮን ግርማ ከጦላይ ማቆያ ማዕከል የተለቀቁ ሁለት እስረኞችን አነጋግራ። ተከታዩን ዘገባ አጠናቅራለች።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ