በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢሕአዴግ “ከመገናኛ ብዙሃን ጋር ለመሥራት ወስኛለሁ፤” አለ


ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ

“ሥራችን ግልጽ እንዲሆን ከተፈለገ፥ የመንግሥትም ሆኑ የግል ሚዲያዎች ሚዛናዊ ዘገባዎችን ማቅረብ አለባቸው። መገናኛ ብዙሃን ለማንኛውም የውጭ ወይም ያስተሳሰብ ተጽዕኖ መጋለጥ የለባቸውም።” የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ።

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ ከአገር ዉስጥም ሆነ ዉጪ አገር የመገናኛ ብዙሃን ጋር ለመስራት በፓርቲያቸው ኢሕአዴግ ጉባኤ ጭምር መወሰናቸውን አስታወቁ።

ኃላፊነት በተሞላበት ሁኔታ እስከሄድን ድረስ ሁላችምም ተጠቃሚዎች እንሆናለን ብለዋል አቶ ኃይለማሪያም። ሰሞኑን ከመንግሥት መገናኛ ብዙሃን ጋር ያደረጉት ቃለ ምልልስ ብዙ ጉዳዮች የተዳሰሱበት ነው።

“ሥራችን ግልጽ እንዲሆን ከተፈለገ፥ የመንግሥትም ሆኑ የግል ሚዲያዎች ሚዛናዊ ዘገባዎችን ማቅረብ አለባቸው፤” ያሉት አቶ ኃይለማሪያም “መገናኛ ብዙሃን ለማንኛውም የውጭ ተጽዕኖ ወይም ያስተሳሰብ ተጽዕኖ መጋለጥ የለባቸውም፤” ሃሳባቸውን ገልጠዋል።

ሥራችን ግልጽ እንዲሆን ከተፈለገ፥ የመንግሥትም ሆኑ የግል ሚዲያዎች ሚዛናዊ ዘገባዎችን ማቅረብ አለባቸው። መገናኛ ብዙሃን ለማንኛውም የውጭ ወይም ያስተሳሰብ ተጽዕኖ መጋለጥ የለባቸውም።
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም በዚሁ ቃለ ምልልስ ከረቤት ሀገሮች ጋር ስላላቸው ግንኙነትም ተናግረዋል። የኤርትራን መንግሥት አሁንም ”በማተራመስ” ባሉት ወንጅለዋል። ደቡብ ሱዳንን በተመለከተም፥ ኢትዮጵያ ከመንግሥትም ሆነ ከተቃዋሚዎች ሳትወግን እንደምታደራድር የተናገሩት።

የዘገባውን ዝርዝር ከዚህ ያድምጡ።

ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማሪም መንግስታቸው ከመገናኛ ብዙኃን ጋር ለመሥራት “አለው” ያሉትን ይህን እቅዳቸውን አስመልክቶ በሰጡት ዙሪያ የመገናኛ ብዙኃኑ አባላትም አስተያየት ሰጥተዋል።

የውጭ መገናኛ ብዙኃን ዘጋቢ ኡመር ረዲን አስተያየት ከዚህ ያድምጡ።

የኢትዮ-ምሕዳሩ ጌታቸው ወርቁን አስተያየት ከዚህ ያድምጡ።

የብሉምበርግ (Bloomberg News) ዘጋቢው ዊልያም ዴቪድሰን (William Davidson) አስተያየት ከዚህ ያድምጡ።

XS
SM
MD
LG