በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጠ/ሚ ዐቢይ በምርጫው ዙሪያ ውይይት አካሄዱ


ፎቶ ፋይል፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ
ፎቶ ፋይል፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ

ቀጣዩ ሃገራዊ ምርጫ እንዲራዘም በፖለቲካ ፓርቲዎች የሚሰነዘሩ ጥያቄዎች ህዝብን የሚያደናግር ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከተፎካካሪ የፖለቲካ ፓቲዎችና ሲቪክ ማኅበራት ጋር በቀጣዩ ምርጫ ዙሪያ ምክክር አድርገዋል፡፡

የመንግሥት መገናና ብዙኃን ምርጫ 2013 ቁልፍ የሽግግር ምዕራፍ የሚል መሪ ሃሳብ ሰንቆ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ጋር ተደርጓል ባሉት ውይይት ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎችና የሲቪክ ማኅበራት ተሳትፈዋል፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት በይፋዊ ገጹ እንዳስታወቀው የውይይቱ ተሳታፊዎች ካነሷቸው ነጥቦች ውስጥ መሰረታዊ ነገሮች ሳይሟሉ ምርጫውን ለማካሄድ መጣደፍ ተገቢ አይደለም የሚለው ይገኝበታል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

ጠ/ሚ ዐቢይ በምርጫው ዙሪያ ውይይት አካሄዱ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:46 0:00

XS
SM
MD
LG