በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"የይግባኝ ውሳኔ ግልባጭ ሳይሰጠን ከሁለት ዓመት በላይ ተቆጥሯል"- የሙስሊም መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴዎች ጠበቃ


በዚህ ምክኒያት ፍትሕ የማግኘት መብታቸው እንደተጣሰና በማረሚያ ቤት ይደርስብናል የሚሉትን በደል እንኳን በአግባቡ ማመልከት እንዳልቻሉ ጠበቃው ገልፀዋል።

በእስር ላይ የሚገኙት አራት የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት በዐሥራ አምስት ቀን ውስጥ ሊያገኙት ይገባ የነበረው የይግባኝ ውሳኔ ግልባጭ ሳይሰጣቸው ሁለት ዓመት መቆጠሩን በጠበቃቸው አማካኝነት ለአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ ገለጹ።

ጠበቃቸው እንደሚሉት፤ በፍርዱ ላይ ይግባኝ ለመጠየቅ የሚያስችለውን የውሳኔ ግልባጭ ለማግኘት ከፍተኛ ጥረት ቢያደርጉም ሊሳካላቸው እንዳልቻለ ተናግረዋል። በተደጋጋሚ ለይግባኝ የቀረቡ ሰነዶች ጠፍተዋል እንደሚባሉም አስረድተዋል። ጽዮን ግርማ ጠበቃዋን ወ/ሮ አዲስ መሐመድን በቅሬታቸው ዙሪያ አነጋግራቸዋለች።

"የይግባኝ ውሳኔ ግልባጭ ሳይሰጠን ከሁለት ዓመት በላይ ተቆጥሯል"- የሙስሊም መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴዎች ጠበቃ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:50 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG