በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የምዕራብ ኢትዮጵያ ኮማንድ ፖስት የኦነግ አባላትን በቁጥጥር ሥር ማዋሉን ገለፀ

የምዕራብ ኢትዮጵያ ኮማንድ ፖስት ወይም እዝ በምዕራብ ኢትዮጵያ ታጥቀው የአካባቢውን ሰላም ሲያውኩ የነበሩ ያላቸውን 835 የኦነግ አባላትን በቁጥጥር ሥር አውያለሁ ማለቱን የኢትዮጵያ የዜና አገልግሎት ዘግቧል።

የምዕራብ ኢትዮጵያ ኮማንድ ፖስት ወይም እዝ በምዕራብ ኢትዮጵያ ታጥቀው የአካባቢውን ሰላም ሲያውኩ የነበሩ ያላቸውን 835 የኦነግ አባላትን በቁጥጥር ሥር አውያለሁ ማለቱን የኢትዮጵያ የዜና አገልግሎት ዘግቧል።

ኮማንድ ፖስቱ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ተስተጓጉለው የነበሩ የመንግሥትና የግል ተቋማትም በአብዛኛው ሥራ መጀመራቸውና የተለያዩ ማኅበራዊና የንግድ እንቅስቃሴዎችም ወደ መደበኛ ተግባራቸው መግባታቸውን ገልጿል።

አያይዞም ኮማንድ ፖስቱ የህዝቡ ተሳትፎ ከዕለት ዕለት ተጠናክሮ ቀጥሏል ይላል። ዕዙ ፀረ ሠላም ኃይሎች ያላቸውን በማጋለጥ ለመንግሥት አካላትና ለኮማንድ ፖስቱ እየጠቆሙና የተዘረፉ ንብረቶች እንዲመለሱ ዕገዛ እያደረጉ ይገኛሉ ማለቱን የኢትዮጵያ የዜና አገልግሎት ገልጿል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG