በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከአስቸጋሪው የየመን ስደት 160 ኢትዮጵያውያን ቢመለሱም በሺዎች የሚቆጠሩ ይቀራሉ


ፍልሰተኞች ከኤደን ወደ አዲስ አበባ ለመመለስ ዝግጅት እያደረጉ
ፍልሰተኞች ከኤደን ወደ አዲስ አበባ ለመመለስ ዝግጅት እያደረጉ

የመን ውስጥ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 160 ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ማክሰኞ ከኤደን ወደ አዲስ አበባ መውሰዱን ዓለም አቀፉ የፍልሰትድርጅት (IOM) አስታወቀ። ይሁን እንጂ አሁንም ኢትዮጵያውያን የሚበዙበት 32 ሺሕ ስደተኞች የመን ውስጥ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ይገኛሉ።

ዓለም አቀፉ የፍልሰት ድርጅት አይ ኦኤም ስደተኞቹን ወደ ሃገራቸው በሰላም እንዲመለሱ ያደረገው ሕገወጥ አዘዋዋሪዎች ስደተኞቹን ወደ ጅቡቲለማሻገር የተጠቀሙበት ጀልባ የኤደን ባህረ ሰላጤ ላይ ተገልብጦ ቢያንስ 42 ሰዎች ህይወታቸው ካለፈ ከአንድ ቀን በኋላ ነው። ጀልባው ወደ 60 የሚጠጉ ሰዎችን አሳፍሮ የነበረ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ በየመን ያለውን ግጭት የሸሹ ከደርዘን በላይ ሕፃናት ይገኙበታል።

ድርጅቱ አያይዞ እደተናገረው በሺዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች እንደ ሶማሊያ እናኢትዮጵያ ካሉ ሀገራት እየተሰደዱ ወደ ሳዑዲ አረቢያ እና በሌሎችየባህረ ሰላጤው አገራት ሥራ ለማግኘት በየዓመቱ አደገኛውን መንገድ ያቋርጣሉ ብሏል።

የድርጅቱ ቃል አቀባይ አንጌላ ዊልስ ብዙዎቹ ድንበሩን አቋርጠው በጭራሽ ያሰቡበት አይደርሱም አብዛኞቹ በየመን እጅግ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥይገኛሉ ብለዋል። በአሁኑ ሰዓትም አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን የሚበዙበት 32 ሺሕ ስደተኞች የመን ውስጥ እንደሚገኙ አያይዘው ተናግረዋል።

“ብዙዎቹ አደገኛ በሆኑ ሁኔታዎች ውስጥ ነው ያሉት፣ መጠለያ ስለሌላቸው መንግድ ላይ ያድራሉ ምንም አይነትአገልግሎትችም አያገኙም። ሌሎችደግሞ በእስር ላይ ናቸው ወይም በህገወጥ አዘዋዋሪዎች ተይዘዋል። በየመን ያሉስደተኞች ጉዳይ እጅግ አሳዛኝ ከመሆኑ የተነሳ ወደ ሀገራቸውለመመለስ ያላቸው አማራጭ ህገ ወጥ አዘዋዋሪዎቹ ብቻእንደሆነ ይሰማቸዋል።” ብለዋል።

እነዚህ ስደተኞች ለዚህ አሰቃቂ እና አብዛኛውን ግዜ በአሳዛኝ ሁኔታ ለሚደመደመው ጉዞ ከፍተኛ ገንዘብ ለአሻጋሪዎች ለመክፈል ይገደዳሉ።አደጋዎች ቢኖሩም ደግሞ ስደተኞቹ ወደ ሃገራቸው ለመመለስ በጣም ይፈልጋሉ። ዌልስ ባለፈው ወር ብቻ ወደ ጅቡቲ በሚወስደው የባህር ጉዞ ላይላይ ቢያንስ 20 ሰዎች መስጠማቸውን ጠቁመዋል።

“እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ከ ግንቦት 2020 ጀምሮ ከ 11 ሺህ በላይ ስደተኞች በህገ ወጥ አዘዋዋሪዎች አማካኝነትአደገኛ የሆነ የጀልባ ጉዞበማድረግ ወደ አፍሪካ ቀንድ ሀገራት ተመልሰዋል። ለመመለስ ፈቃደኛ የሆኑትን ሰዎችየሚያግዘው የዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት ፕሮግራምከየመን መውጣት ላቃታቸው መውጫ መንገድ ያዘጋጃል።ስለዚህ በነዚህ መንገዶች ላይ የሚግኙ ሀገራት መንግስታቶች ይህን ጥረታችንንእንዲደግፉና ስደተኞቹ ደህንነታቸውተጠብቆ ወደ ሀገራቸው የሚመለሱበትን ሁነታ ለመፍጠር እንዲተባበሩ ጥሪያችንን እናቀርባለን።”

አይ.ኦ.ኤም ከጥቅምት ወር ጀምሮ በየመን የሚገኙና ወደ ሃገራቸው ለመመለስ የሚፈልጉ ከ6000 በላይ ስደተኞችን መመዝገቡን አስታውቋል።በተጨማሪም በሺዎች የሚቆጠሩ ሰነድ አልባ ስደተኞች ዜግነታቸው እስኪረጋገጥ እና ለጉዞ የሚያስፈልጋቸውን ሰነድ እየተጠባበቁ የሚገኙስደተኞች ይገኛሉ። እነርሱም ሰነድ ያገኙና አንድ ቀን ወደ ሃገራቸው ይጓዛሉ።

(በሊሳሽ ላይን ከጄኔቫ ለተጠናቀረው ዘገባ ጽዮን ግርማ ወደ አማርኛ መልሳዋለች)

ከአስቸጋሪው የየመን ስደት 160 ኢትዮጵያውያን ቢመለሱም በሺዎች የሚቆጠሩ ይቀራሉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:58 0:00


XS
SM
MD
LG