No media source currently available
በታንዛኒያ በህገ ወጥ ጉዞ ላይ ተይዘዉ በእሥር ላይ የነበሩ 108 የኢትዮጵያ ዜጎች ዛሬ ወደ ሀገር መመለሱን በታንዛኒያ የኢትዮጵያ ኢምባሲ አስታወቀ። በኢምባሲዉ የኢትዮጵያ መንግሥት ዲፕሎማት አቶ ቴዎድሮስ ግርማ ኢትዮጵያዊያኑ ከ2 እስከ 4 ዓመት በእሥር የቆዩ መሆናቸውን ለአሜርካ ድምፅ ተናግረዋል።