በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞች የተሳፈሩበት ጀልባ ተገልብጦ ሰባት ስዎች ሞቱ


Tanzania
Tanzania

ሰባት ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞች የተሳፈሩበት ጀልባ ታንዛኒያ ጠረፍ ህንድ ውቅያኖስ ውስጥ ተገልብጦ መሞታቸው ተገለጠ።

ሰባት ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞች የተሳፈሩበት ጀልባ ታንዛኒያ ጠረፍ ህንድ ውቅያኖስ ውስጥ ተገልብጦ መሞታቸው ተገለጠ።

የሰሜናዊ ታንጋ ክፍለ ግዛት ፖሊስ አዛዥ ለሮይተርስ እንደገለጡት ጀልባው አሥራ ሁለት ኢትዮጵያውያን አሳፍሮ ሲጓዝ ነው የተገለበጠው። አምስቱን ተሳፋሪዎች በህይወት ለማውጣት እንደተቻለ የገለፁት የታንዛኒያው ፖሊስ አዛዥ የጀልባው ካፒቴን አልተገኘም ብለዋል።

የታንዜኒያ የኢሚግሬሽን አገልግሎት ስለሞቱት ሰዎች የቀብር አፈፃፀም ጉዳይ ከኢትዮጵያ ኤምባሲ ጋር እየተነጋገረ መሆኑን ነው የፖሊስ አዛዡ የገለፁት። በህይወት የተረፉት ሰዎች ጀልባው የተገለበጠው ወደደቡብ አፍሪካ በመጓዝ ላይ እያለ መሆኑን እንደገለፁ አክለዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG