ዋሽንግተን ዲሲ —
አናንያ ሶሪና ኤልያስ ገብሩ የተባሉ ሁለት ጋዜጠኞችና የኢንተርኔት አምደኞች ክስ ሳይመሰረትባቸውና የታሰሩበትን ምክንያት በይፋ ሳይነገራቸው ከሦስት ወር በላይ በእስር ቤት እንደሚገኙ ቤተሰቦቻቸው ለአሜሪካ ድምጽ ገለጹ። ወጣቶቹ በጹሑፍ ሐሳባቸውን ከመግለጽ ውጭ የሠሩት ወንጀል የለም ብለዋል - ቤተሰቦቻቸው።
መንግሥት በበኩሉ የታሰሩ ካሉ ወይ ሞያው የሚጠይቀውን የጋዜጠኝነት ሥነ ምግባር ባለማክበራቸው ነው ወይም ጋዜጠኞች ባለመሆናቸው ነው ብሏል።
የጋዜጠኞች ደህንነት ተሟጋቹ ሲፒጄ ጋዜጠኞች እና ጦማሪያ የታሰሩት ስለፃፉ ብቻ ነው በአስቸኳይ ሊፈቱ ይገባል ማለቱ ይታወሳል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ