በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከሳዑዲ የተመለሱ ኢትዮጵያውያን ምን ይጠብቃቸዋል?


በለጥያቄዎ መልስ ዝግጅት ተሳታፊዎች፤ የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ መለስ ዓለም፣ ከዚህ ቀደም ከሳዑዲ የተመለሱ ኢትዮጵያውያን ላይ ያተኮረ ጥናት ያደረጉት የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የማኅበረሠብ ሳይኮሎጂ መምህር ዶክተር አበባው ምናየ ከአዲስ አበባና የዶቼቬሌ ራዲዮ ዘጋቢ ስለሺ ሽብሩ ከሪያድ ናቸው፡፡

የሳዑዲ አረቢያ መንግሥት የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸው ባዕዳን ሠራተኞች ከሀገሩ እንዲወጡ ያስቀመጠው የዘጠና ቀናት የጊዜ ገደብ ከተጠናቀቀ በኋላ የሳዑዲ መንግሥት እንደገና የ30 ቀናት ተጨማሪ ጊዜ ሰጥቷል።

ከሳዑዲ የተመለሱ ኢትዮጵያውያን ምን ይጠብቃቸዋል?
please wait

No media source currently available

0:00 0:47:14 0:00

የኢትዮጵያ መንግሥት በሰጠው መረጃ እስካሁን ከ40 ሺሕ በላይ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገር የተመለሱ ሲሆን ዝግጅት አጠናቀው በአይሮፕላን አቅርቦትና በተለያዩ ምክንያቶች መብረር ያልቻሉና የሚንገላቱ በርካቶች እንደሆኑ ይታወቃል፡፡

በሌላ በኩል 20 ሺሕ የሚደርሱ ከአሠሪዎቻቸው ጋር በመጋጨት፣ በሕገወጥነትና በልዩ ልዩ ወንጀሎች ተይዘው እስር ቤት እንደሚገኙ፤ እንዲሁም ከ250 ሺሕ በላይ የሚሆኑና ስለ ምሕረት ዐዋጁ መንም መረጃ የሌላቸውወይንም ወደ ኢትዮጵያ መመለስ የማይፈለጉ በርካታ ዜጎች እንዳሉ ታውቋል፡፡

በዚህ ሂደት አለፈው የተመልሱትን ምን ይጠብቃቸዋል? የዛሬው የጥያቄዎ መልስ መወያያ ርዕሰ ጉዳይ ነው። ተመላሾቹን ተቀብሎ ከማኅበረሠቡ ጋር ለማዋሃድና በሥራ ለማሰማራትስ ምን ዝግጅት ተደርጓል? የሚሉና ሌሎችም ነጥቦች ተነስተዋል፡፡

በለጥያቄዎ መልስ ዝግጅት ተሳታፊዎች የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ መለስ ዓለም፣ ከዚህ ቀደም ከሳዑዲ የተመለሱ ኢትዮጵያውያን ላይ ያተኮረ ጥናት ያደረጉት የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የማኅበረሠብ ሳይኮሎጂ መምህር ዶክተር አበባው ምናየ ከአዲስ አበባ፣ የዶቼቬሌ ራዲዮ ዘጋቢ ስለሺ ሽብሩ ከሪያድ በውይይቱ ላይ ተሳትፈዋል፡፡

አዘጋጅና አቅራቢ ትዝታ በላቸው ናት።

ውይይቱን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG