በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ወጣቱ የቪዲቸር ቴክኖሎጂ ድርጅት ባለቤት ኬብሮን ደጀኔ


የቪዲቸር ቴክኖሎጂ ኩባንያ ሥራ አስፈጻሚ፣ መስራችና ባለቤት የሆነው የ32 ዓመቱ ወጣት ኬብሮን ደጀኔ
የቪዲቸር ቴክኖሎጂ ኩባንያ ሥራ አስፈጻሚ፣ መስራችና ባለቤት የሆነው የ32 ዓመቱ ወጣት ኬብሮን ደጀኔ

ኬብሮን ደጀኔ አሁን ወደ 32ኛ ዓመቱ እየተጠጋ ያለ ወጣት ነው፡፡ ይህን ቪዲቸር የሚባል የቴክኖሎጂ ድርጅት ካሊፎርኒያ ውስጥ ሲሊከን ቫሊ በተሰኘው የቴክኖሎጂ መናኻሪያ ውስጥ የዛሬ አራት ዓመት ሲያቋቁም ገና 30 ዓመት እንኳ ያልሞላው ወጣት ነበር፡፡ ዛሬ ድርጅቱን በዓለም አስፋፍቶ ከአሜሪካ ካናዳ አውሮፓ ሲሪላናካ ሳይቀር ባለሙያዎችን ቀጥሮ የሚያስራ ሰው ሆኗል፡፡ የቪዲቸር ኩባንያ ሥራ አስፈጻሚ መስራችና ባለቤት የሆነው ኬብሮንን ይበልጥ ደስ የሚያሰኘው ግን እሱም ሆነ ባለሙያዎችን ያሰባሰበው ድርጅቱ የሚሰሩት በወጣትነቱ ለተለያት አገሩ ኢትዮጵያ መሆኑ ነው፡፡

ኬብሮን ደጀኔ በውጭ አገር የሚገኙ ትውልደ ኢትዮጵያውያን፣ በየአካባቢያቸው የሚገኙ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎችን በመጠቀም ከአገራቸው ጋር የሚያገናኝዋቸውን ጉዳዮች በቀላሉ መፈጸም እንዲችሉ የሚያግዝ ቴኮኖሎጂ እንዲመቻች አድርጓል፡፡

ቪዲቸር የተሰኘውን የቴክኖሎጂ ከሚያከናውናቸው ዘርፈ ብዙ አገልግሎቶች መካከል ፣ የፍርድ ቤት ውክልና፣ ፖስፖርት ፣ መታወቂያና የተለያዩ የባንክና የጉዞ ሰነዶችን በርቀት ሆኖ በመፈረም፣ ከየትኛውም የዓለም ክፍል በቀላሉና በፍጥነት መቀባበል የሚያስችል ቴክኖሎጂ የሚገኝበት መሆኑን ኬብሮን ይናገራል፡፡

ከዚህ በፊት ወራትና ቀናትን ይፈጁ የነበሩ ጉዳዮች ዛሬ በደቂቃና ሰዓታት ውስጥ የሚጠናቀቁ መሆኑንም ኬብሮን ይገልጻል፡፡

የተለያዩ የመንግሥት ተቋማትን ወደ አንድ ቋት በማምጣት፣ ባለጉዳዮች የትም መሄድ ሳያስፈልጋቸው ስልኮቻቸው ላይ ሆነው በአጭር ጊዜ ውስጥ ጉዳዮቻቸውን እንዲያከናውኑ ማድረጉንም ኬብሮን ተናግሯል፡፡

በ18 ዓመቱ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ የመጣው ኬብሮን ቀደም ሲል የሚኖረው በካሊፎርኒያ አካባቢ ሲሆን አሁን ግን መኖሪያውን በቨርጂኒያ አርሊንግተን አድርጎ ወደ ኢትዮጵያ እየተመላለሰ እንደሚሰራ ገልጿል፡፡

ድርጅቱ ቪዲቸር ከሚሰራቸው ሥራዎች መካከል ዋነኛው በውጭ አገር ያሉ ኢትዮጵያውያን በአገራቸው ውስጥ ያሉ ጉዳዮቻቸውን ለማስፈጸም በአካል መገኘት ሳያፈልጋቸው፣ ሳምንታትና ወራትን መቆየትም ሳያሻቸው፣ በጥቂት ሰዓታትና ደቂቃዎች ውስጥ ጉዳዮቻቸውን ማቀላጠፍ የሚያስችላቸውን ቴክኖሎጂ መዘርጋት ነው፡፡

በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆናቸውን የገለጸው ኬብሮን በዓለም ላይ በዓይነቱ የመጀመሪያው የሆነውን ቴክኖሎጂ ኢትዮጵያ ውስጥ ወደሚገኙ የተለያዩ የመንግሥትና ማህበራዊ ተቋማት እንዲሁም ወደ ሌሎቹ አፍሪካ አገሮችም ለማስገባት እየሠራና አንዳንዶቹም በዝግጅት ላይ መሆናቸውን አስረድቷል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

ወጣቱ የቪደቸር ቴክኖሎጂ ድርጅት ባለቤት ኬብሮን ደጀኔ
please wait

No media source currently available

0:00 0:13:35 0:00


XS
SM
MD
LG