በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአትላንታ ኢትዮጵያ ህብረተሰብ፣ ለማዕከሉ የ1.7 ሚሊዮን ዶላር ይዞታ ገዛ


የአትላንታ ህብረተሰብ ማዕከል የቦርድ አባላት
የአትላንታ ህብረተሰብ ማዕከል የቦርድ አባላት

ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በጆርጂያ ክፍለ ግዛት የአትላንታ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ማዕከል፣ አትላንታ ከተማ ውስጥ 1.7 ሚሊዮን ዶላር በሚሆን ወጭ ለህብረተሰቡ አገልግሎት የሚሰጥ አንድ ሥፍራ መግዛቱን አስታውቋል፡፡

በአስር ኤከር ላይ ያረፈው የማዕከሉ አዲሱ ይዞታ
በአስር ኤከር ላይ ያረፈው የማዕከሉ አዲሱ ይዞታ

በአስር ኤከር ላይ የተንጣለለው ይዞታው ከ20ሺ በላይ ሰዎችን የሚይዝ መናፈሻ ያለው ሲሆን ከ2ሺ በላይ የሚሆኑ ሰዎች ሊሰበሰቡት የሚችል አዳራሽም አለው፡፡

ወደ 15 የሚሆኑን የቢሮ አገልግሎት የሚውሉ ክፍሎች እንዳሉትም የአትላንታ ህብረተሰብ ማዕክል ዳይሬክተር አቶ አቶ ዮናስ ታምሩ ለአሜሪካ ድምጽ ተናግረዋል፡፡

እንደ ወትሮው ሁሉ ሰሞኑንም በኢትዮጵያ ተጎጂ ለሆኑ ወገኖቹ በቅርቡ በ100ሺ የሚቆጠር ገንዘብ ልኳል ያሉት አቶ ዮናስ ፣ ይህንንም ማዕከል ለመግዛት የአትላንታ ኢትዮጵያውያን፣ እንዲሁም የእምነትና የንግድ ተቋማት ወጭውን ሙሉ ለሙሉ የሸፈኑት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

አዲሱ የማዕከሉ ህንፃ
አዲሱ የማዕከሉ ህንፃ

ዳሬክተሩ በቅርቡ ይመረቃል ያሉት ማዕክል እስከዛሬ ለተለያዩ ዝግጅቶች በተለይም ለስቴዲዮም የምንከፈለውን እስከ 20ሺ ዶላር የሚቆጠረውን ወጭ ያስቀርልናል ብለዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

የአትላንታ ኢትዮጵያ ህብረተሰብ፣ ለማዕከሉ የ1.7 ሚሊዮን ዶላር ይዞታ ገዛ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:28 0:00


XS
SM
MD
LG