ናይሮቢ —
በህገ ወጥ ጉዞ ላይ ተይዘው ታንዛኒያ እሥር ቤት የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ከሁለት ሺህ በላይ እንደሚሆኑ በታንዛኒያ የኢትዮጵያ ኢምባሲ አስታወቀ። በኢምባሲዉ የዲያስፖራ ክፍል ምክትል ፀኃፊ አቶ ምስጋናዉ መሸሻ ኢትዮጵያዊያኑ ያሉበትን እሥር ቤት መለየት ላይ መሆናቸዉን ነው ለአሜርካ ድምፅ የገለጹት። አሁንም ኢምባሲው በታንዛኒያ በገሞዮ በምትባል ግዛት የእሥር ጊዜያቸዉን ጨርሰዉ ያሉ ኢትዮጵያዊያንን ወደ ሀገር ለመለስ ከዓለምቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት /IOM/ ጋር እየሰራ መሆኑን ገልጿል።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ