No media source currently available
የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ከአርቲስት ሀጫሉ ግድያ ወዲህ በተለያዩ ምክንያቶች በአዲስ አበባ የታሰሩ የፖለቲካ እሰረኞችንና ጋዜጠኞችን በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ስር በሚገኝ የታሳሪዎች ማቆያ ቦታ ድረስ በመሄድ የጎበኝዋቸውና በርካታዎቹንም ያነጋገሯቸው መሆኑን ለአሜሪካ ድምጽ ተናግረዋል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ እነ አቶ ጅዋር መሃመድ፣ በቀለ ገርባ፣ እስክንድር ነጋ የመሳሰሉት ይገኙበታል፡፡