ዋሺንግተን ዲሲ —
ዉጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ፕሬዚደንት ኦባማ ኢትዮጵያ ባደረገችዉ የኢኮኖሚ እድገት አመስግነዉ ይቀራሉ ባሉዋቸዉ የዴሞክራዊ ሂደቶች የወዳጅ ምክር ለግሰዋል ብለዋል።
ፕሬዚደንት ኦባማ ጋዜጠኞች በነጻነት ስራቸዉና ካልሰሩና ተቃዋሚ ፓርቲዎች ገደብ ሳይደረግባቸዉ ህዝቡን ካላደራጁ ብዙሃኑ የኢትዮጵያ ሕዝብ የኢትዮጵያ እድገት ተጠቃሚ እንደማይሆን ገልጸዋል።
ዉጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ለአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ በሰጡት ቃለ ምልልስ ግን የኢትዮጵያ ዴሞክራሲ በጅምር ደረጃ እንደሚገኝ ጠቁመዉ፣ ድርጅታቸዉ ኢህአዴግ ሂደቱን ለማሻሻል ጥረት እንደሚደርግ ተናግረዋል። ጋዜጠኞች ወንጀል ካልሰሩ እንደማይታሰሩ ገልጸዉ፥ እርስ በርስ ባለመተባበር ተቃዋሚዎችን ነቅፈዋል። ኢህአዴግ ተቃዋሚዎችን ሳይቀር አግባብ ባለዉ መንገድ እንደሚያዝ በመግለጽ እስር ቤት ያሉት የግንቦት ሰባት ዋና ጸሐፊ አቶ አንዳርጋቸዉ ጽጌ ከእስር ቤት ዉጭ ኢትዮጵያ በልማት ያደረገችዉን እድገት ለማየት እድል እንደተሰጣቸዉና መጽሐፍ ለመድረስም እንደበቁ ተናግረዋል።
ሙሉዉን ቃለ ምልልስ ያድምጡ