ዋሺንግተን ዲሲ —
ባለፈው ሐሙስ በዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምበሲ፣ ዶ/ር አዲሱ ገብረ/እግዚአብሄር የኢትዮጵያ ሠብዓዊ መብት ከሚሽን ኰሚሽነር፣ የአገሪቱን የመብት አያያዝ ሪፖርት ያቀረቡበት አንድ ስብሰባ ተካሂዶ ነበር።
ስብሰባውን የጠራው በኢትዮጵያ መንግሥት ተቀጥሮ ይሠራል የተባለው/SGRLLC/ የተባለው ሎቢስት/አግባቢ/ ቡድን መሆኑም ታውቋል።
በስብሰባው ላይ ለመገኘት ከሄዱ ኢትዮጵያውያን መካከል አንዳንዶቹ ከገቡ በኋላ እንዲወጡ የተደረጉ ሲሆን፣ ሌሎች ደግሞ ከብዙ ጭቅጭቅ በኋላ ቢገቡም ጥያቄ የማቅረብ ዕድል እንደተነፈጉ ተናግረዋል።
የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡