በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያዊቱ ዶ/ር ሰገነት ቀለሙ በዩኔስኮ ተሸለሙ


ዶ/ር ሰገነት ቀለሙ
ዶ/ር ሰገነት ቀለሙ


ዶ/ር ሰገነት ቀለሙ በምርምር ላይ
ዶ/ር ሰገነት ቀለሙ በምርምር ላይ

please wait

No media source currently available

0:00 0:03:13 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሣይንስና የባህል ድርጅት - ዩኔስኮ ሎሬአል ከሚባል ዓለምአቀፍ የውበትና የሠውነት ጥራት መጠበቂያ አቅርቦቶች አምራች ቡድን ጋር በየዓመቱ የሚያካሂደው ሴቶች በሣይንስ ሽልማት ኢትዮጵያዊቱ ዶ/ር ሰገነት ቀለሙ አሸናፊ ሆኑ፡፡

ሣይንቲስቷ ዶ/ር ሰገነት ቀለሙ ተቀማጭነቱ ናይሮቢ - ኬንያ የሆነው የነፍሣት አካላት እና አካባቢ ጥናት ዓለምአቀፍ ማዕከል /ኢሲፔ/ (International Center for Insect Physiology and Ecology - ICIPE) ዋና ዳይሬክተር ናቸው፡፡

ዶ/ር ሰገነት ከትናንት በስተያ (ረቡዕ) ፈረንሣይ ዋና ከተማ ፓሪስ ላይ በተካሄደው የዓለምአቀፍ ሽልማት ሥነ-ሥርዓት ላይ ለዘንድሮው16ኛው የዩኔስኮ እና ሎሬአል ሽልማት በአሸናፊነት ከቀረቡት መካከል አንዷ ናቸው፡፡
ዶ/ር ሰገነት ቀለሙ - በድርጅታቸው ደጃፍ ከባልደረቦቻቸው ጋር
ዶ/ር ሰገነት ቀለሙ - በድርጅታቸው ደጃፍ ከባልደረቦቻቸው ጋር

ዶ/ር ሰገነት እና የምርምር ቡድናቸው ኮሎምቢያ ሳሉ ከአፍሪካ የተወሰደ ብራኪያርያ የሚባል የሰርዶ ዘር የሆነና ለከብቶች መኖነት የሚውል ሣር በሽታንና የተፈጥሮ መለዋወጥን መቋቋም በሚችልበት ሁኔታ አሻሽለውታል፡፡

ዛሬ ይህ የሣር ዓይነት በመላው ዓለም ተስፋፍቶ እንደሚገኝና ጥቅሙም የበረከተ ወተት በመስጠት፣ የስጋ ምርትን በማብዛት እጅግ የበዛ መሆኑን ዶ/ር ሰገነት አብራርተዋል፡፡

ዶ/ር ሰገነት የብዙ ዓለምአቀፍ ሽልማቶች ባለቤት ሲሆኑ እርሣቸው በተሸለሙ ቁጥር ደስ የሚላቸው ኢትዮጵያም አብራ ስለምትጠራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ዶ/ር ሰገነት በከትናንት በስተያው አምስት ሴት ሣይንቲስቶች የተሸለሙበት የሎሬአል-ዩኔስኮ ሽልማት የመቶ ሺህ ዶላር ሥጦታ በግል የሚያስገኝላቸው ሲሆን ስማቸው የተቀረፀበት የብር ዋንጫም ተሰጥቷቸዋል፡፡

ጎጃም - ፍኖተሰላም ተወልደው ያደጉ፣ ትምህርታቸውንም ፍኖተሰላም፣ ደብረማርቆስ፣ አዲስ አበባና ሃሮማያ፣ በውጭም ሜክሲኮና ዩናይትድ ስቴትስ የተከታተሉ ሲሆኑ በአሜካና በአፍሪካ ሃገሮች ለብዙ ዓመታት ሠርተዋል፡፡
ዶ/ር ሰገነት ቀለሙ
ዶ/ር ሰገነት ቀለሙ

ተጨማሪ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
XS
SM
MD
LG